ምሳሌ 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታምነህ ኑር፥ በራስህም ጥበብ አትደገፍ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፍጹም ልብህ በጌታ ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሙሉ ልብህ በእግዚአብሔር ታመን እንጂ በራስህ ዕውቀት አትመካ። |
እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።”
ደመናው ድንኳኑን በጋረደበት ቀን ቍጥር ሁሉ የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ቃል ይሰፍሩ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር።
ደመናውም እስከ ወር ቈይቶ በድንኳኑ ላይ ቢቀመጥ የእስራኤል ልጆች በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፤ አይጓዙምም ነበር፤ ነገር ግን በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።
እርስ በርሳችሁም በአንድ ዐሳብ ተስማሙ፤ ትዕቢትን ግን አታስቡ፤ ራሱን የሚያዋርደውንም ሰው ምሰሉ፤ እና ዐዋቆች ነን አትበሉ።