ምሳሌ 17:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መማለጃን በዐመፃ በብብቱ የሚቀበል መንገዶቹን አያቀናም፥ ክፉ ሰውም ከጽድቅ መንገዶች ይርቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው ፍትሕ ለማዛባት፣ በስውር ጕቦ ይቀበላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀጥእ የፍርድን መንገድ ለማጥመም ከብብት መማለጃን ይወስዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰው ፍርድን ለማጣመም፥ በምሥጢር ጉቦ ይቀበላል። |
አለቆችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፤ ፍርድንም ሊያጣምሙ ይፈልጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይፈርዱም፤ የመበለቲቱንም አቤቱታ አያዳምጡም።
በአንቺ ውስጥ ደምን ያፈስሱ ዘንድ መማለጃን ተቀበሉ፤ በአንቺም አራጣና ትርፍ ወስደዋል፤ ቀማኛነትሽንና ኀጢአትሽን ፈጸምሽ፤ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሱ ዘንድ፥ ነፍሶችንም ያጠፉ ዘንድ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው።
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህም አታድላ፤ ጉቦን አትቀበል፥ ጉቦ የጥበበኞችን ዐይን ያሳውራልና፥ የእውነትንም ቃል ያጣምማልና ጉቦ አትቀበል።
እነሆኝ፥ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንንስ አህያ ወሰድሁ? ማንንስ ሸነገልሁ? በማንስ ላይ ግፍ አደረግሁ? ነጠላ ጫማ እንኳን ቢሆን ከማን እጅ መማለጃ ተቀበልሁ? መስክሩብኝ፤ እኔ እመልስላችኋለሁ።”