ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ምሳሌ 16:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅንነትን የሚሹ ሰላምን ያገኛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው መንገድ እግዚአብሔርን ደስ ሲያሠኘው፣ ጠላቶቹ እንኳ ዐብረውት በሰላም እንዲኖሩ ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው አካሄድ ጌታን ደስ ያሰኘው እንደሆነ፥ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው በአካሄዱ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ከሆነ ከጠላቶቹ ጋር እንኳ በሰላም እንዲኖር ያደርገዋል። |
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
አለውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ታግለህ በርትተሃልና።”
በይሁዳም ዙሪያ በነበሩ የምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ድንጋጤ ሆነ፤ ከኢዮሳፍጥም ጋር አልተዋጉም።
የንጉሡንም ትእዛዝ በወንዙ ማዶ ላሉት ለንጉሡ ሹሞችና ገዢዎች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት አከበሩ።
አቤቱ! በመከራቸውና በጭንቃቸው ጊዜ በጠላቶቻቸው ዘንድ ስለ እነርሱ በጎ ነገር በአንተ ፊት የቆምሁ ባልሆን ይህ ለእነርሱ መከናወን ይሁን።
ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበዛልኝማል፤ የመዓዛ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን፥ ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ አሟልቻለሁ።
ወደ እግዚአብሔር በሚገባችሁ ትሄዱ ዘንድ፥ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ፥ እግዚአብሔርንም በማወቅ እያደጋችሁ፥ በሁሉ ደስ ታሰኙት ዘንድ።
የሰላም አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘለዓለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።