የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፤ የገዥ ውድቀት ግን በሕዝብ ማነስ ነው።
የሕዝብ ብዛት የንጉሥ ክብር ሲሆን፣ የዜጎች ማነስ ግን ለገዥ መጥፊያው ነው።
የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፥ በሰው ጥቂትነት ግን የገዥ ጥፋት አለ።
የንጉሥ ታላቅነት የሚለካው በሚያስተዳድራቸው ሕዝብ ብዛት ነው፤ የሚገዛው ሕዝብ ከሌለው ግን ለንጉሡ ጥፋት ነው።
አሁንም ተነሥተህ ወጥተህ ለአገልጋዮችህ በልባቸው የሚገባ ነገር ንገራቸው። ዛሬ ወደ እነርሱ ካልወጣህ በዚች ሌሊት አንድ ሰው ስንኳ ከአንተ ጋር የሚያድር እንዳይኖር በእግዚአብሔር እምላለሁ፤ ከሕፃንነትህ ጀምሮ እስከዚች ቀን ድረስ ካገኘህ መከራ ሁሉ ዛሬ የምታገኝህ መከራ እንድትከፋብህ እንግዲህ አንተ ለራስህ ዕወቅ” አለው።
ኢዮአብም ንጉሡን፥ “የጌታዬ የንጉሡ ዐይን እያየ አምላክህ እግዚአብሔር ዛሬ ካለው ሕዝብ መጠን በላይ መቶ እጥፍ ይጨምርበት፤ ጌታዬ ንጉሡ ግን ይህን ነገር ለምን ይፈልጋል?” አለው።
አክዓብም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ ደነገጠ፤ ልብሱንም ቀደደ፤ እያለቀሰም ሄደ፤ በሰውነቱም ላይ ማቅ ለበሰ፤ ጾመም፤ ኢይዝራኤላዊው ናቡቴንም በገደለበት ቀን ደግሞ ማቅ ለብሶ ነበር።
ለኢዮአካዝም ከኀምሳ ፈረሰኞች፥ ከዐሥርም ሰረገሎች፥ ከዐሥር ሺህም እግረኞች በቀር ሕዝብ አልቀረለትም፤ የሶርያ ንጉሥ አጥፍቶአቸዋልና፥ በአውድማም እንዳለ ዕብቅ አድቅቆአቸዋልና።
ነገር ግን እንዳስጨነቁአቸው መጠን እንዲሁ በዙ፤ እጅግም ጸኑ ፤ ግብፃውያንም የእስራኤልን ልጆች ይጸየፉአቸው ነበር።
ፈርዖንም፥ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፤ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት አድኑአት” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።
የእግዚአብሔር ትእዛዝ የሕይወት ምንጭ ነው። ሰዎችንም ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጡ ያደርጋል።
ትዕግሥተኛ ሰው ጥበብ የበዛለት ይሆናል፤ ትዕግሥት የጐደለው ሰው ግን ሰነፍ ነው፤
ኢየሩሳሌም ሆይ! ዐይንሽን አንሥተሽ እነዚህን ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቺ፤ ለአንቺ የሰጠሁሽ መንጋ፤ የክብር በጎችሽ ወዴት አሉ?