Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 14:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ትዕግሥተኛ ሰው ጥበብ የበዛለት ይሆናል፤ ትዕግሥት የጐደለው ሰው ግን ሰነፍ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ታጋሽ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ ግልፍተኛ ሰው ግን ቂልነትን ያሳያል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው፥ ቁጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ትዕግሥተኛ ብትሆን አስተዋይ መሆንህን ትገልጣለህ፤ ቊጡ ብትሆን ግን ስንፍናህን ታሳያለህ።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 14:29
20 Referencias Cruzadas  

ቍጡ ሰው ያለምክር ይሠራል፤ ብልህ ግን ብዙ ይታገሣል።


የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፤ የገዥ ውድቀት ግን በሕዝብ ማነስ ነው።


ቍጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ትዕግሥተኛ ሰው ግን የሆነውን ስንኳ ያጠፋል። ትዕግሥተኛ ሰው ክርክርን ያጠፋል፥ ኀጢአተኛ ሰው ግን ጠብን ፈጽሞ ያነሣል።


ትዕግሥተኛ ሰው ከኀያል፥ ጥበብ ያለው ሰውም ሰፊ ርስት ካለው፥ በመንፈሱ የሠለጠነ ሰውም ሀገርን ከሚገዛ ሰው ይሻላል።


ሻካራ ቃልን ከመናገር የሚከለክል ዐዋቂ ነው፥ ትዕግሥተኛ ሰውም ብልህ ነው።


ይቅር ባይ ሰው ይታገሣል፥ መመካቱም ኀጢአተኞችን ይቃወማቸዋል፥


ጠብቃት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አክብራት፥ እርስዋም ታቅፍሃለች።


ሰነፍ በታ​ላቅ ማዕ​ርግ ላይ ተሾመ፥ ባለ​ጠ​ጎች ግን በተ​ዋ​ረደ ስፍራ ተቀ​መጡ።


የነ​ገር ፍጻሜ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ይሻ​ላል፤ ታጋ​ሽም ከልብ ትዕ​ቢ​ተኛ ይሻ​ላል።


በመ​ን​ፈ​ስህ ለቍጣ ችኩል አት​ሁን፥ ቍጣ በሰ​ነ​ፎች ብብት ያር​ፋ​ልና።


ሙሴም በም​ድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ የዋህ ሰው ነበረ።


ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤


ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።


ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos