La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 11:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጻድቅ ልጅ ለሕይወት ይወለዳል፤ የኃጥኣን መወለድ ግን ለሞት ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እውነተኛ ጻድቅ ሕይወትን ያገኛል፤ ክፋትን የሚከተል ግን ወደ ሞቱ ይጓዛል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በጽድቅ የሚጸና በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፥ ክፋትን የሚከተል ግን ወደ ሞት ይሄዳል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መልካም ሥራ ለመሥራት ቊርጥ ውሳኔ ያደረገ ሰው በሕይወት ይኖራል፤ ስሕተት በማድረግ የሚጸና ግን ይሞታል።

Ver Capítulo



ምሳሌ 11:19
18 Referencias Cruzadas  

ኤል​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ለምን ላክህ? በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም” አለው።


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም በላ​ቸው” አለው። ኤል​ያ​ስም ሄደ፤ እን​ዲ​ሁም ነገ​ራ​ቸው።


የጻድቃን ሥራ ሕይወትን ያደርጋል፤ የኃጥኣን ፍሬ ግን ኀጢአት ነው።


በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች። ጻድቅ በሞተ ጊዜ ጸጸትን ይተዋል፥ የኀጢአተኛ ሞት ግን በእጅ የተያዘና ሣቅ ይሆናል።


በጽድቅ መንገድ ሕይወት አለ፥ ክፉን የሚያስቡ ሰዎች መንገዶች ግን ወደ ሞት ያወርዳሉ።


እግዚአብሔርን መፍራት የሰው ሕይወት ነው፤ የማይፈራው ግን ዕውቀት በሌለበት ቦታ ውስጥ ይኖራል።


ከጽድቅ መንገድ የሚሳሳት ሰው፥ በረዐይት ጉባኤ ያርፋል።


ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ክብርን ያገኛል።


በእኔ ላይ በደልን የሚፈጽሙ ራሳቸውን ይበድላሉ፤ የሚጠሉኝም ሞትን ይወድዳሉ።


ነገር ግን በሕ​ዝብ ሁሉ ዘንድ እር​ሱን የሚ​ፈ​ራና እው​ነ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ በእ​ርሱ ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነው።


የኀ​ጢ​አት ትር​ፍዋ ሞት ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ነው።


በሕ​ይ​ወት ትኖር ዘንድ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ሰ​ጥ​ህን ምድር ትወ​ርስ ዘንድ እው​ነ​ተ​ኛ​ውን ፍርድ ተከ​ተል።


ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።


የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።


ልጆች ሆይ፥ ማንም አያስታችሁ፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው።