Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 21:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ክብርን ያገኛል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ጽድቅንና ፍቅርን የሚከተል፤ ሕይወትን ብልጽግናንና ክብርን ያገኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ጽድቅን ክብርንም ያገኛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ጽድቅንና ቸርነትን የሚከተል ሰው ሕይወትን፥ ብልጽግናንና ክብርን ያገኛል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 21:21
19 Referencias Cruzadas  

ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ይጠግባሉና።


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የጸ​ና​ች​ሁና የማ​ት​ና​ወጡ ሁኑ፤ ዘወ​ትር በጎ ምግ​ባ​ርን አብ​ዝ​ታ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አበ​ር​ክቱ፤ ስለ ጌታ​ችን መድ​ከ​ማ​ችሁ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ይ​ደለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


እግዚአብሔርን መፍራት፥ ጥበብን ባለጠግነትንና ክብርን፥ ሕይወትንም ትወልዳለች።


ከሁሉ ጋር ወደ ሰላም ሩጡ፤ ቅድ​ስ​ና​ች​ሁ​ንም አት​ተዉ፤ ያለ እርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​የው የለም።


አንተ ግን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።


የክፉዎች መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ ጽድቅን የሚከተሉትን ግን እግዚአብሔር ይወድዳቸዋል።


ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፤ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።


እና​ንተ ጽድ​ቅን የም​ት​ከ​ተሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ትሹ፥ ስሙኝ፤ የተ​ቈ​ረ​ጣ​ች​ሁ​በ​ትን ጽኑዕ ዓለት የተ​ቈ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ባ​ት​ንም ጥልቅ ጕድ​ጓድ ተመ​ል​ከቱ።


አሁ​ንም ወን​ድ​ማ​ችን ይታ​ነጽ ዘንድ ሰላ​ምን እን​ከ​ተ​ላት።


ነገር ግን ይህን ፈጽሜ የተ​ቀ​በ​ልሁ አይ​ደ​ለም፤ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ እኔን የመ​ረ​ጠ​በ​ትን አገኝ ዘንድ እሮ​ጣ​ለሁ እንጂ።


እን​ወ​ቀው፤ እና​ው​ቀ​ውም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ከ​ተል፤ እንደ ወገ​ግ​ታም ተዘ​ጋ​ጅቶ እና​ገ​ኘ​ዋ​ለን፤ በም​ድ​ርም ላይ እንደ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውና እንደ ኋለ​ኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመ​ጣል።


ነፍስህ ትድን ዘንድ፥ ለአንገትህም ሞገስ ይሆንህ ዘንድ። ለሥጋህ ፈውስ፥ ለአጥንትህም ጠገን ይሆንልሃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ልዑል ነው፥ ክብ​ሩም ከሰ​ማ​ያት በላይ ነው።


የጻድቃን ሥራ ሕይወትን ያደርጋል፤ የኃጥኣን ፍሬ ግን ኀጢአት ነው።


ጻድቅ ልጅ ለሕይወት ይወለዳል፤ የኃጥኣን መወለድ ግን ለሞት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios