La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በሲና ምድረ በዳ ፋሲ​ካን አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረጉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም በመጀመሪያው ወር፣ በዐሥራ አራተኛውም ቀን ፀሓይ በምትጠልቅበት ጊዜ በሲና ምድረ በዳ ፋሲካ አደረጉ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉንም አደረጉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመጀመሪያውም ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በሲና ምድረ በዳ የፋሲካን በዓል አከበሩ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን በምሽት በሲና ምድረ በዳ በዓሉን አከበሩ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረጉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በሲና ምድረ በዳ ፋሲካን አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ።

Ver Capítulo



ዘኍል 9:5
18 Referencias Cruzadas  

ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ፤ እን​ዲሁ አደ​ረገ።


ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘዘ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


እን​ዲ​ሁም የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ሁሉ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሥራ​ውን ሁሉ ሠሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙ​ሴና ለአ​ሮን ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ነገ​ራ​ቸው።


ሙሴና አሮን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እን​ዲሁ በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ስለ ሌዋ​ው​ያን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረ​ጉ​ላ​ቸው።


ሙሴም ፋሲ​ካን ያደ​ርጉ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገ​ራ​ቸው።


እና​ን​ተስ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ ካደ​ረ​ጋ​ችሁ ወዳ​ጆች ናችሁ።


“አሁ​ንም ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ ከሰ​ማይ የተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ኝን ራእይ አል​ካ​ድ​ሁም።


በአ​ር​ባ​ኛው ዓመት በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን፥ ሙሴ እን​ዲ​ነ​ግ​ራ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገ​ራ​ቸው፤


እነሆ፥ እና​ንተ ገብ​ታ​ችሁ በም​ት​ወ​ር​ሱ​አት ምድር ውስጥ እን​ዲህ ታደ​ርጉ ዘንድ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘኝ ሥር​ዐ​ትና ፍር​ድን አሳ​የ​ኋ​ችሁ።


አብ​ር​ሃም በተ​ጠራ ጊዜ ርስት አድ​ርጎ ይወ​ር​ሰው ዘንድ ወዳ​ለው ሀገር ለመ​ሄድ በእ​ም​ነት ታዘዘ፤ ወዴት እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስም ሳያ​ውቅ ሄደ።


ሙሴስ በኋላ ስለ​ሚ​ነ​ገ​ረው ነገር ምስ​ክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታ​መነ ነበረ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ፤ ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ ምዕ​ራብ ፋሲ​ካን አደ​ረጉ።