Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እና​ን​ተስ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ ካደ​ረ​ጋ​ችሁ ወዳ​ጆች ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የማዝዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እናንተም እኔ የማዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 15:14
19 Referencias Cruzadas  

በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና፤” አለ።


ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።


መጽሐፍም “አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት፤” ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።


ትእ​ዛዜ በእ​ርሱ ዘንድ ያለ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውም የሚ​ወ​ደኝ እርሱ ነው፤ የሚ​ወ​ደ​ኝ​ንም አባቴ ይወ​ደ​ዋል፤ እኔም እወ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ራሴ​ንም እገ​ል​ጥ​ለ​ታ​ለሁ።”


“ከወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ኝስ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ።


ለእ​ና​ንተ ለወ​ዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ሥጋ​ች​ሁን የሚ​ገ​ድ​ሉ​ትን አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ ከዚ​ህም የበ​ለጠ ማድ​ረግ የሚ​ች​ሉት የላ​ቸ​ውም።


ይህ​ንም ዐው​ቃ​ችሁ ብት​ሠሩ ብፁ​ዓን ናችሁ።


ባሪ​ያዬ እስ​ራ​ኤል፥ የመ​ረ​ጥ​ሁህ ያዕ​ቆብ፥ የወ​ዳጄ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ሆይ፥


እና​ቱም ለአ​ሳ​ላ​ፊ​ዎቹ፥ “የሚ​ላ​ች​ሁን ሁሉ አድ​ርጉ” አለ​ቻ​ቸው።


እኔ እን​ደ​ም​ሄድ ወደ እና​ን​ተም እን​ደ​ም​መ​ለስ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን ሰም​ታ​ች​ኋል፤ ብት​ወ​ዱ​ኝስ ወደ አብ በመ​ሄዴ ደስ ባላ​ችሁ ነበር፤ እርሱ አብ ይበ​ል​ጠ​ኛ​ልና።


አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በዚህ ምድር የነ​በ​ሩ​ትን አሕ​ዛብ ከሕ​ዝ​ብህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ያሳ​ደ​ድህ፥ ለወ​ዳ​ጅ​ህም ለአ​ብ​ር​ሃም ዘር ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሰ​ጠ​ሃት አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?


እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከር​ቤ​ዬን ከሽ​ቱዬ ጋር ለቀ​ምሁ፥ እን​ጀ​ራ​ዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወ​ይን ጠጄን ከወ​ተቴ ጋር ጠጣሁ። ባል​ን​ጀ​ሮች በሉ፥ ጠገ​ቡም፤ የወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ጠጡ፥ ሰከ​ሩም፥ ልባ​ቸው የጠፋ ነውና።


ሙሴና አሮ​ንም እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ።


ወደ አውድማውም ወረደች፥ አማትዋም ያዘዘቻትን ሁሉ አደረገች።


የና​ታ​ንም ልጅ ኦርኒያ የሹ​ሞች አለቃ ነበረ፤ የና​ታ​ንም ልጅ ዘባት የን​ጉሡ አማ​ካ​ሪና ወዳጅ ነበረ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተከ​ተለ፤ እር​ሱ​ንም ከመ​ከ​ተል አል​ራ​ቀም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዛ​ቱን ጠበቀ።


እነ​ር​ሱም ገብ​ተው ወረ​ሱ​አት፤ ነገር ግን ቃል​ህን አል​ሰ​ሙም፤ በሕ​ግ​ህም አል​ሄ​ዱም፤ ያደ​ር​ጉም ዘንድ ካዘ​ዝ​ሃ​ቸው ሁሉ ምንም አላ​ደ​ረ​ጉም፤ ስለ​ዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ህ​ባ​ቸው።


እን​ዳ​ዘ​ዘ​ኝም አደ​ረ​ግሁ፤ ቀን ለቀ​ንም እክ​ቴን እንደ ስደ​ተኛ እክት አወ​ጣሁ፤ በማ​ታም ጊዜ ግን​ቡን በእጄ ነደ​ልሁ፤ በጨ​ለ​ማም አወ​ጣ​ሁት፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም በት​ከ​ሻዬ ላይ አን​ግቼ ተሸ​ከ​ም​ሁት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios