ይስሐቅም የአባቱ የአብርሃም አገልጋዮች ቈፍረዋቸው የነበሩትን የውኃ ጕድጓዶች ደግሞ አስቈፈረ፤ አባቱ አብርሃም ከሞተ በኋላ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፍነዋቸው ነበርና፤ አባቱም አብርሃም ይጠራቸው በነበረው ስም ጠራቸው።
ዘኍል 32:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህንም የሠሩአቸውን ከተሞች በየስማቸው ጠሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ስማቸው የተለወጠውን ናባውን፣ በኣልሜዎንን፣ ሴባማንን ዐደሱ፤ ላደሷቸውም ከተሞች ስም አወጡላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስማቸውም የተለወጠውን ናባውን፥ በኣልሜዎንን፥ ሴባማን ነበር፤ እነዚህንም የሠሩአቸውን ከተሞች በሌላ ስም ጠሩአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የነቦን፥ በኋላ ስሙ የተለወጠው የባዓልመዖንንና የሲብማን ከተሞች አደሰ፤ እነርሱም ላደሱአቸው ከተሞች ሁሉ አዲስ ስም አወጡላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቂርያትይምን፥ ስማቸውም የተለወጠውን ናባውን፥ በኣልሜዎንን፥ ሴባማን ሠሩ፤ እነዚህንም የሠሩአቸውን ከተሞች በሌላ ስም ጠሩአቸው። |
ይስሐቅም የአባቱ የአብርሃም አገልጋዮች ቈፍረዋቸው የነበሩትን የውኃ ጕድጓዶች ደግሞ አስቈፈረ፤ አባቱ አብርሃም ከሞተ በኋላ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፍነዋቸው ነበርና፤ አባቱም አብርሃም ይጠራቸው በነበረው ስም ጠራቸው።
የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች አዝነዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች እስከ ኢያዜር ደርሰው ወደ ምድረ በዳ ወጥተው ነበር፤ ቍጥቋጦቹም ተዘርግተው ባሕርን ተሻግረው ነበር።
ቤል ወደቀ፤ ዳጎን ተሰባበረ፤ ምስሎቻቸውም እንደ ትቢያ ሆኑ፤ አራዊትና እንስሳም ይረግጡአቸዋል፤ እንደ ፋንድያም ሸክም የሚያጸይፉ ናቸውና አያነሡአቸውም።
ስለ ሞአብ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍታለችና ወዮላት! ቂርያታይም አፍራለች፤ ተይዛማለች፤ መጠጊያዋም አፍራለች፤ ደንግጣማለች።
ስለዚህ እነሆ የሞአብን ጫንቃ ከከተሞቹ፥ በዳርቻው ካሉት የምድሩ ትምክሕት ከሆኑት ከተሞቹ፥ ከቤትየሺሞት፥ ከባኣልሜዎን፥ ከቂርያታይም አደክማለሁ።
ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም እንደ ተጨመረ፥ በወጣህበት ተራራ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተጨመር፤
በእናንተም መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ፤ የአማልክቶቻቸውም ስሞች በእናንተ መካከል አይጠሩ፤ አትማሉባቸውም፤ አታምልኳቸውም፤ አትስገዱላቸውም፤