Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 46:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ቤል ወደቀ፤ ዳጎን ተሰ​ባ​በረ፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ሆኑ፤ አራ​ዊ​ትና እን​ስ​ሳም ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ እንደ ፋን​ድ​ያም ሸክም የሚ​ያ​ጸ​ይፉ ናቸ​ውና አያ​ነ​ሡ​አ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ቤል ተዋረደ፤ ናባው እጅግ ዝቅ አለ፤ ጣዖቶቻቸው በአጋሰስ ተጭነዋል፤ ይዘዋቸው የሚዞሩት ምስሎች ሸክም ናቸው፤ ለደከሙ እንስሳት ከባድ ጭነት ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ቤል ተዋረደ፥ ናባው ተሰባበረ፤ ጣዖቶቻቸው በእንስሳና በከብት ላይ ተጭነዋል፤ ሸክሞቻችሁ ለደካማ እንስሳ ከባድ ጭነት ሆነዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “ቤልና ኔቦ የተባሉት የሐሰት አማልክት ያጐነብሳሉ፤ ጣዖቶቻቸው በጭነት እንስሶች ላይ ተጭነዋል፤ የተጫኑት ምስሎች ለደካማ እንስሳ ከባዶች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ቤል ተዋረደ፥ ናባው ተሰባበረ፥ ጣዖቶቻቸው በእንስሳና በከብት ላይ ተጭነዋል፥ ሸክሞቻችሁ ለደካማ እንስሳ ከባድ ጭነት ሆነዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 46:1
22 Referencias Cruzadas  

ጕል​በ​ቱስ ብርቱ ስለ​ሆነ ትታ​መ​ነ​ዋ​ለ​ህን? ተግ​ባ​ር​ህ​ንስ ለእ​ርሱ ትተ​ዋ​ለ​ህን?


እኔም በዚ​ያች ሌሊት በግ​ብፅ ሀገር አል​ፋ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ከሰው እስከ እን​ስሳ ድረስ በኵ​ርን ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም አማ​ል​ክት ሁሉ ላይ በቀ​ልን አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


በእጅ የተ​ሠሩ ጣዖ​ታ​ትን ሁሉ ይሰ​ው​ራሉ፤


በዚ​ያም ቀን ሰው ይሰ​ግ​ድ​ላ​ቸው ዘንድ ያበ​ጁ​አ​ቸ​ውን የብ​ሩ​ንና የወ​ር​ቁን ጣዖ​ቶ​ቹን ለፍ​ል​ፈ​ልና ለሌ​ሊት ወፍ ይጥ​ላል።


እነ​ሆም፥ በፈ​ረ​ሶች የሚ​ቀ​መጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚ​ሄዱ ፈረ​ሰ​ኞች ይመ​ጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እር​ሱም መልሶ፥ “ባቢ​ሎን ወደ​ቀች! ወደ​ቀች! ጣዖ​ቶ​ች​ዋም ሁሉ፥ የእ​ጆ​ች​ዋም ሥራ​ዎች ሁሉ በም​ድር ላይ ተጥ​ለው ደቀቁ” አለ።


ተባ​ትና እን​ስት አን​በሳ፥ እፉ​ኝ​ትም፥ ነዘር እባ​ብም፥ በሚ​ወ​ጡ​ባት በመ​ከ​ራና በጭ​ን​ቀት ምድር በኩል ብል​ጽ​ግ​ና​ቸ​ውን በአ​ህ​ዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛ​ግ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በግ​መ​ሎች ሻኛ ላይ እየ​ጫኑ ወደ​ማ​ይ​ጠ​ቅ​ሙ​አ​ቸው ሕዝብ ይሄ​ዳሉ።


እና​ንተ ከአ​ሕ​ዛብ ወገን ሆና​ችሁ ያመ​ለ​ጣ​ችሁ፥ ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ኑ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ተማ​ከሩ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን የም​ስ​ላ​ቸ​ውን እን​ጨት የሚ​ሸ​ከ​ሙና ያድን ዘንድ ወደ​ማ​ይ​ችል አም​ላክ የሚ​ጸ​ልዩ ዕው​ቀት የላ​ቸ​ውም።


በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ተሸ​ክ​መ​ውት ይሄ​ዳሉ፤ በስ​ፍ​ራ​ውም በአ​ኖ​ሩት ጊዜ በዚያ ይቆ​ማል፤ ከስ​ፍ​ራ​ውም ፈቀቅ አይ​ልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮህ አይ​ሰ​ማ​ውም፤ ከክ​ፉም አያ​ድ​ነ​ውም።


እንደ ተቀ​ረጸ ብር ናቸው፤ እነ​ር​ሱም አይ​ና​ገ​ሩም፤ መራ​መ​ድም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል። ክፉ መሥ​ራ​ትም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፥ ደግ​ሞም መል​ካም ይሠሩ ዘንድ አይ​ች​ሉ​ምና አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው።”


“ለአ​ሕ​ዛብ ተና​ገሩ፤ አው​ሩም፤ ዓላ​ማ​ው​ንም አንሡ፥ አት​ደ​ብቁ፦ ባቢ​ሎን ተያ​ዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮ​ዳክ ፈራች፤ ምስ​ሎ​ች​ዋም አፈሩ፤ ጣዖ​ታ​ቷም ደነ​ገጡ፤ በሉ።


እር​ስዋ የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች ምድር ናትና፥ እነ​ር​ሱም በደ​ሴ​ቶ​ችዋ ይመ​ካ​ሉና ሰይፍ በው​ኆ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ር​ቃሉ።


በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ የዋ​ጠ​ች​ው​ንም ከአ​ፍዋ አስ​ተ​ፋ​ታ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብም ከዚያ ወዲያ ወደ እር​ስዋ አይ​ሰ​በ​ሰ​ቡም፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ቅጥ​ሮች ይወ​ድ​ቃሉ።


ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን የባ​ቢ​ሎ​ንን ምስ​ሎች የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፤ ምድ​ር​ዋም ሁሉ ትደ​ር​ቃ​ለች፤ ተዋ​ግ​ተ​ውም የሞ​ቱት ሁሉ በመ​ካ​ከ​ልዋ ይወ​ድ​ቃሉ።


ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ች​ዋን የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በም​ድ​ር​ዋም ሁሉ የተ​ገ​ደ​ሉት ይወ​ድ​ቃሉ።


እግዚአብሔርም ከስምህ ማንም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይዘራ ስለ አንተ አዝዞአል፣ ከአምላኮችህ ቤት የተቀረጸውንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል አጠፋለሁ። አንተም የተጠቃህ ነህና መቃብርህን እምሳለሁ።


እነ​ዚ​ህ​ንም የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች በየ​ስ​ማ​ቸው ጠሩ​አ​ቸው።


ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፤ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም።


በነ​ጋ​ውም የአ​ዛ​ጦን ሰዎች ማለዱ፤ ወደ ዳጎ​ንም ቤት ገቡ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ አገ​ኙት፤ ዳጎ​ን​ንም አን​ሥ​ተው በስ​ፍ​ራው አቆ​ሙት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos