በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን፥ ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾምን አወጅሁ።
ዘኍል 30:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስእለቷን ሁሉ፥ ነፍስዋንም የሚያዋርደውን የመሐላ ማሰሪያ ሁሉ ባልዋ ያጸናዋል፤ ወይም ባልዋ ይከለክለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የትኛውንም ስእለቷን ወይም ራሷን ለመከላከል በመሐላ የታሰረችበትን ሁሉ ባሏ ሊያጸናው ወይም ሊያፈርሰው ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስእለትዋን ሁሉ ራስዋንም የሚያዋርደውን መሐላ ሁሉ ባልዋ ያጸናዋል፥ ባልዋም ከንቱ ያደርገዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባልዋ ማንኛውንም ስእለት ሆነ መሐላ የመፍቀድ ወይም የመቃወም መብት አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስእለትዋን ሁሉ ነፍስዋንም የሚያዋርደውን መሐላ ሁሉ ባልዋ ያጸናዋል፥ ባልዋም ከንቱ ያደርገዋል። |
በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን፥ ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾምን አወጅሁ።
እኔ ይህን ጾም የመረጥሁ አይደለሁም፤ እንደዚችም ባለች ቀን ሰው ራሱን ቢያሳዝን፥ አንገቱንም እንደ ቀለበት ቢያቀጥን፥ ማቅ ለብሶ በአመድ ላይ ቢተኛም፥ ይህ ጾም በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠ አይደለም።
“በዚህ በሰባተኛው ወር ዐሥረኛዋ ቀን የማስተስረያ ቀን ናት፤ ቅድስት ጉባኤ ትሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁን አስጨንቋት፤ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ።
የዕረፍት ሰንበት ትሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁንም አዋርዱ፤ በወሩ በዘጠነኛው ቀን ከማታ ጀምራችሁ እስከ ዐሥረኛው ቀን ማታ ድረስ፥ ሰንበታችሁን አድርጉ።”
“የዚህም ወር ዐሥረኛዋ ቀን ለእናንተ የተቀደሰች ትሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁን አስጨንቁአት፤ ከሥራ ሁሉ ምንም አታድርጉ።
ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ስእለቷን ቢከለክላት፥ ስለ ስእለቷ ወይም ራስዋን ስላሰረችበት መሐላ ከአፍዋ የወጣው ነገር አይጸናም፤ ባልዋ ከልክሏታል፤ እግዚአብሔርም ያነጻታል።
ነገር ግን በየዕለቱ ዝም ቢላት፥ ስእለቷን ሁሉ፥ በእርስዋም ላይ ያለውን መሐላ ሁሉ ያጸናዋል፤ በሰማበት ቀን ዝም ብሎአታልና አጽንቶታል።
ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራሱ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስዋ ወንድ፤ የክርስቶስም ራሱ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወድዳለሁ።
ለጸሎት እንድትተጉ ከምትስማሙበት ጊዜ ብቻ በቀር፥ ባልና ሚስት አትለያዩ፤ ዳግመኛ ሰይጣን ድል እንዳያደርጋችሁ በአንድነት ኑሩ፤ ሰውነታችሁ ደካማ ነውና ።