የመጀመሪያዪቱ ቀን ቅድስት ትባላላች፤ እንዲሁም ሰባተኛዋ ቀን ቅድስት ትሁንላችሁ፤ ለነፍስ ከሚሠራው ሥራ ሁሉ በቀር ማናቸውንም ሥራ ሁሉ አትሥሩ
ዘኍል 28:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባተኛውም ቀን የተቀደሰ ይሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ተግባርም አትሥሩበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰባተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰባተኛው ቀን ለአምልኮ ትሰበሰባላችሁ፤ በእርሱ ምንም ሥራ አትሠሩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰባተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። |
የመጀመሪያዪቱ ቀን ቅድስት ትባላላች፤ እንዲሁም ሰባተኛዋ ቀን ቅድስት ትሁንላችሁ፤ ለነፍስ ከሚሠራው ሥራ ሁሉ በቀር ማናቸውንም ሥራ ሁሉ አትሥሩ
ያችንም ቀን ቅድስት ጉባኤ ብላችሁ ታውጃላችሁ፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አታድርጉባት፤ በምትቀመጡበት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዐት ነው።
ስድስት ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው፤ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ጉባኤ ይሆንበታል፤ ምንም ሥራ አትሠሩም፤ በምትኖሩበት ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው።
ሰባት ቀንም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ ሰባተኛዋ ቀን ቅድስት ጉባኤ ትሁንላችሁ፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አትሥሩባት።”
“በበዓለ ሠዊት ቀን በሰንበታት በዓላችሁ አዲሱን የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ባቀረባችሁ ጊዜ፥ የተቀደሰ ቀን ይሆንላችኋል፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።
“በሰባተኛውም ወር ከወሩ የመጀመሪያዋ ቀን ለእናንተ ይህች ዕለት የተቀደሰች ናት፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩባት፤ ምልክት ያለባት ቀን ትሁንላችሁ።
“በሰባተኛውም ወር ዐሥራ አምስተኛዋ ቀን ለእናንተ የተቀደሰች ትሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩባት፤ ሰባት ቀንም ለእግዚአብሔር በዓል አድርጉ።
ስድስት ቀን ቂጣ እንጀራ ብላ፤ ሰባተኛው ቀን ግን መውጫው ስለሆነ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በዓል ይሁን፤ ለነፍስም ከሚሠራው በቀር ሥራን ሁሉ አታድርግበት።