ዘኍል 26:55 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ምድሪቱ በየስማቸው በዕጣ ትከፋፈላለች፤ እንደ አባቶቻቸው ነገድ ይወርሳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመሬት ድልድሉም በዕጣ ይሁን፤ እያንዳንዱ የሚወርሰውም በየነገድ አባቶቹ ስም ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፋፈላለች፤ እንደ አባቶቻቸው ነገድ ስም ይወርሳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም ክፍፍሉ የሚደረገው በዕጣ ነው፤ ዕጣውም የሚጣለው በየነገዱ መሠረት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፈላለች፤ እንደ አባቶቻቸው ነገድ ስም ይወርሳሉ። |
ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጡ፥ በእናንተም መካከል ልጆችን ለሚወልዱ መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ትካፈሉአታላችሁ፤ እነርሱም በእስራኤል ልጆች መካከል እንደ አሉ የሀገር ልጆች ይሆኑላችኋል፤ በእስራኤልም ነገዶች መካከል ከእናንተ ጋር ርስትን ይወርሳሉ።
ምድሪቱንም ትወርሳላችሁ፤ በየወገኖቻችሁም ትከፋፈሏታላችሁ፤ ለብዙዎች ድርሻቸውን አብዙላቸው፤ ለጥቂቶችም ድርሻቸውን ጥቂት አድርጉ፤ እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደቀለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ።
ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፥ “እግዚአብሔር ለዘጠኙ ነገድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ይሰጡአቸው ዘንድ እንደ አዘዘ በዕጣ የምትወርሱአት ምድር ይህች ናት፤
“ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርጎ በዕጣ ከፍሎ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር ጌታችንን አዘዘው፤ እግዚአብሔርም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ ይሰጣቸው ዘንድ ጌታችንን አዘዘው።
እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደ ክፍላቸው በየነገዳቸው ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።
የዮሴፍም ልጆች ኢያሱን፥ “እኛ ብዙ ሕዝብ ስንሆን እስከ አሁንም እግዚአብሔር ስለ ባረከን ለምን አንድ ክፍል፥ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸን?” ብለው ወቀሱት።
እናንተም ምድሪቱን በሰባት ክፍል ክፈሏት፤ ወደ እኔም ወዲህ አምጡልኝ፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት በዚህ ዕጣ አጣጥላችኋለሁ።