Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 26:55 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

55 ሆኖም ክፍፍሉ የሚደረገው በዕጣ ነው፤ ዕጣውም የሚጣለው በየነገዱ መሠረት ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

55 የመሬት ድልድሉም በዕጣ ይሁን፤ እያንዳንዱ የሚወርሰውም በየነገድ አባቶቹ ስም ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

55 ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፋፈላለች፤ እንደ አባቶቻቸው ነገድ ስም ይወርሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

55 ነገር ግን ምድ​ሪቱ በየ​ስ​ማ​ቸው በዕጣ ትከ​ፋ​ፈ​ላ​ለች፤ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ነገድ ይወ​ር​ሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

55 ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፈላለች፤ እንደ አባቶቻቸው ነገድ ስም ይወርሳሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 26:55
21 Referencias Cruzadas  

ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ለዘጠኝ ተኩል ነገዶች እንዲሰጥ እግዚአብሔር ያዘዘው በዕጣ የምትካፈሉት ርስት ይህ ነው።


ምድሪቱንም በተለያዩት ነገዶችና ጐሣዎች መካከል በዕጣ ተከፋፈሉ፤ የጐሣው ቊጥር ከፍ ላለው ሰፊ መሬት ይሰጠው፤ የጐሣው ቊጥር አነስተኛ ለሆነው ደግሞ ጠበብ ያለ መሬት ይሰጠው። እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣው እንደ ወጣለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ምድሪቱን በርስትነት ትረከባላችሁ።


እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ ያለው ግዛት በሙሉ ለዘጠኙ ነገድ ተኩል በዕጣ ተከፈለ።


እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኢያሱ ምድሩን ሁሉ በእጁ አደረገ፤ ለእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ድርሻ ርስት አድርጎ በመስጠት ለእስራኤላውያን በሙሉ አከፋፈለ። ስለዚህም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።


ደግሞም በብርሃን መንግሥት ውስጥ ከቅዱሳን ጋር ርስት እንድትካፈሉ ያበቃችሁን እግዚአብሔር አብን በደስታ አመስግኑት።


ዕጣም በጣሉ ጊዜ ዕጣው ለማትያስ ወጣ፤ ስለዚህ እርሱ ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቈጠረ።


ዕጣ መጣል ጠብን ያበርዳል፤ ሁለት ጠንካራ ተከራካሪዎችንም ይገላግላል።


ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ዕጣ ይጥላሉ፤ ነገር ግን ውሳኔውን የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው።


ሰባተኛው ዕጣ ለዳን ነገድ በየወገኖቻቸው የተሰጠው የርስት ድርሻ ነበር፤


ስድስተኛው ዕጣ ለንፍታሌም ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤


አምስተኛው ዕጣ ለአሴር ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤


አራተኛው ዕጣ ለይሳኮር ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤


ሦስተኛው ዕጣ ለዛብሎን ነገድ በየወገናቸው ወጣ፤ እነርሱም የተቀበሉት ርስት እስከ ሣሪድ ይደርሳል፤


ሁለተኛው ዕጣ ለስምዖን ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ ርስቱም ለይሁዳ ነገድ እስከ ተመደበው ምድር ድረስ ገባ ያለ ነበር፤


የእነዚህን ሰባት ክፍያዎች የሚገልጠውንም ማስረጃ በጽሑፍ አድርጋችሁ አምጡልኝ፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ዕጣ እጥልላችኋለሁ።


የዮሴፍ ነገድ ወደ ኢያሱ ቀርበው “እግዚአብሔር ባርኮን ለበዛነው ለእኛ እንዴት አንድ ዕጣ ብቻ ሰጠኸን?” ብለው ጠየቁት።


ዕጣ የሚጣለውም ከፍተኛ ቊጥርና አነስተኛ ቊጥር ባላቸው ቤተሰቦች መካከል ነው።”


ዘላቂ ርስትም ትሁንላችሁ፤ ልጆች ወልደው በመካከላችሁ የሚኖሩ ባዕዳንም ምድሪቱን በምትካፈሉበት ጊዜ የራሳቸው ድርሻ ይኑራቸው፤ እንደማንኛውም እስራኤላውያን ዜጋ ተቈጥረው ምድሪቱን ከሚካፈሉት ከእስራኤል ነገዶች ጋር ዕጣ እንዲጣልላቸው ያስፈልጋል።


“ምድሪቱን በዕጣ ለእስራኤል ሕዝብ እንድታከፋፍል እግዚአብሔር አንተን ጌታችንን አዞሃል፤ እንዲሁም የዘመዳችንን የጸሎፍሐድን ድርሻ ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አዞሃል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios