እግዚአብሔርም አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማኅፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይወለዳሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።”
ዘኍል 20:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፥ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ያገኘንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ከቃዴስ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ሲል መልእክተኞች ላከ፤ “ወንድምህ እስራኤል የሚለው ይህ ነው፤ የደረሰብን መከራ ሁሉ ምን እንደ ሆነ አንተም ታውቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ የደረሰብንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ከቃዴስ ላከ፤ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ በእኛ ላይ የደረሰውን ችግር ሁሉ ሰምተሃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፦ ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ያገኘንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤ |
እግዚአብሔርም አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማኅፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይወለዳሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።”
ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፤ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙንም ያዕቆብ ብላ ጠራችው። ርብቃ ዔሳውንና ያዕቆብን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።
ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖንና በግብፃውያን ላይ ስለ እስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ በመንገድም ያገኛቸውን ድካም ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እንደ አዳናቸው ለአማቱ ነገረው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦“ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፥ በምድር ላይም ማኅፀንን አርክሶአልና፥ የሚዘልፈውንና የሚያስደነግጠውን በርብሮአልና፥ መዓቱንም ለዘለዓለም ጠብቆአልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የኤዶምያስ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም።
ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እናንተ ግን፦ በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ።
ገሥግሠውም በቃዴስ ፋራን ምድረ በዳ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ደረሱ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።
ከግብፅ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት፥ እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።
ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፥ “እግዚአብሔር ምድሪቱን አሳልፎ እንደ ሰጣችሁ ዐወቅሁ፤ እግዚአብሔር እናንተን መፍራትን በላያችን አምጥትዋልና፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ የተነሣ ቀልጠዋልና።
በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞሬዎን ነገሥት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን፥ በአስታሮትና በኤድራይን በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል።
እነርሱም አሉት፥ “በአምላክህ በእግዚአብሔር ስም እጅግ ከራቀ ሀገር ባሪያዎችህ መጥተናል፤ ዝናውንም፥ በግብፃውያንም ያደረገውን ሁሉ፥