ዘኍል 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰው በቤት ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፤ ወደ ቤት የሚገባ ሁሉ በቤቱም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው በድንኳን ውስጥ በሚሞትበት ጊዜ የሚፈጸመው ሥርዐት የሚከተለው ነው፤ ወደ ድንኳኑ የሚገባም ሆነ በዚያ ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው እስከ ሰባት ቀን ድረስ የረከሰ ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሰው በድንኳን ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፤ ወደ ድንኳኑ የሚገባ ሁሉ በድንኳኑም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው በድንኳኑ ውስጥ በሚሞትበት ጊዜ ተፈጻሚ የሚሆነው ሕግ ይህ ነው። እርሱ በሞተበት ጊዜ በዚያ ድንኳን ውስጥ ያለ ሰው ወይም ወደዚያ የሚገባ ሰው ለሰባት ቀን ያልነጻ ሆኖ ይቈያል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው በድንኳን ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፤ ወደ ድንኳኑ የሚገባ ሁሉ በድንኳኑም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። |
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፥ “ከወገናቸው በሞተ ሰው ራሳቸውን እንዳያረክሱ ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው።
የሞተውን ሰው በድን የነካ ሁለመናውን ባያነጻ የእግዚአብሔርን ድንኳን ያረክሳል፤ ያ ሰው ከእስራኤል ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል፤ በእርሱም ላይ የሚያነጻ ውኃ አልተረጨምና ርኩስ ይሆናል፤ ርኵሰቱ ገና በእርሱ ላይ ነው።
“የእስራኤል ልጆች ለምጻሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ በሰውነቱ የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤
“ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት የራሱ ብፅዐት ይረክሳል፤ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጭ፤ በሰባተኛው ቀን ይላጨው።