ልያም፥ “ባሌን መውሰድሽ አይበቃሽምን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይደር” አለች፤ ሰጠቻትም።
ዘኍል 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር ለይቶ የመረጣችሁን፥ የእግዚአብሔርን ድንኳን አገልግሎት ትሠሩ ዘንድ፥ እንድታገለግሉአቸውም በማኅበሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀረባችሁን ታሳንሱታላችሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል አምላክ እናንተን ከቀሩት እስራኤላውያን ማኅበረ ሰብ መለየቱና በእግዚአብሔር ማደሪያ አገልግሎት እንድትፈጽሙ ወደ ራሱ ማቅረቡ፣ እንድታገለግሏቸውም በማኅበረ ሰቡ ፊት እንድትቆሙ ማድረጉ አይበቃችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር የለያችሁ፥ የጌታንም ማደሪያ አገልግሎት እንድትሠሩ፥ እንድታገለግሉአቸውም በማኅበሩ ፊት እንድትቆሙ ወደ እርሱ ለማቅረብ መፍቀዱን እንደ ቀላል ነገር ቈጠራችሁትን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እርሱ ቀርባችሁ በማደሪያው ድንኳን አገልግሎታችሁን እንድትፈጽሙና በፊታቸውም ቆማችሁ የእስራኤልን ጉባኤ እንድታገለግሉ የእስራኤል አምላክ ከሌላው የእስራኤል ማኅበር መካከል መርጦ እናንተ የተለያችሁ እንድትሆኑ ማድረጉን እንደ ቀላል ነገር ታዩታላችሁን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር የለያችሁ፥ የእግዚአብሔርንም ማደሪያ አገልግሎት ትሠሩ ዘንድ፥ እንድታገለግሉአቸውም በማኅበሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀረባችሁ አይበቃችሁምን? |
ልያም፥ “ባሌን መውሰድሽ አይበቃሽምን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይደር” አለች፤ ሰጠቻትም።
ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ እኔ በፊትህ እጅግ ታናሽ ስሆን ስለ ባሪያህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህ የሰው ሕግ ነው።
በእስራኤልም ሁሉ መሥራት የሚችሉትን ሌዋውያን ራሳቸውን ለእግዚአብሔር እንዲያነጹና ቅድስቲቱንም ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ እንዲያኖሩ አዘዛቸው። ንጉሡም ኢዮስያስ አለ፥ “በትከሻችሁ የምትሸከሙት አንዳች ነገር አይኑር፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ፤
የይሁዳም ሕዝብ በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለቀዳምያት፥ ለዐሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎችን ሾሙ።
እርሱም አለ፥ “እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፥ ስሙ፤ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን? እግዚአብሔርን ታደክማላችሁ፤
የቀረውን ማሰማርያችሁን በእግራችሁ የረገጣችሁት፥ የተሰማራችሁበት መልካሙ መሰማርያ ባይበቃችሁ ነውን? የቀረውንስ ውኃ በእግራችሁ ያደፈረሳችሁት፥ ጥሩውን ውኃ መጠጣታችሁ ባይበቃችሁ ነውን?
ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ላይ ዕዳ እንዳይሆንባቸው ሌዋውያን በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስፈሩ፤ ሌዋውያን የምስክሩን ድንኳን ሕግ ይጠብቁ።”
በምድረ በዳ ትገድለን ዘንድ፥ በእኛም ላይ አለቃችን ትሆን ዘንድ ወተትና ማር ከምታፈስሰው ምድር ያወጣኸን አነሰህን?
ሌዋውያንንም ወደ ወንድምህ ወደ አሮንና ወደ ልጆቹ ወደ ካህናቱ ታገባቸዋለህ። ከእስራኤል ልጆች ተለይተው ለእኔ ሀብት ሆነው ተሰጥተዋልና።
የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ፥ ሲጾሙም መንፈስ ቅዱስ፥ “በርናባስንና ሳውልን እኔ ለፈለግኋቸው ሥራ ለዩልኝ” አላቸው።
ለእኔስ በእናንተ ዘንድ መመስገን ውርደት ነው፤ ጻድቅ ብትሉኝ፥ በመዋቲ ሰው ዘንድም ቸር ብላችሁ ብታከብሩኝ እኔ ለራሴ አልፈርድም።
በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸከም ዘንድ፥ እርሱንም ለማገልገል በእግዚአብሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስሙም ይባርክ ዘንድ እግዚአብሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ።
የሳኦልም ብላቴኖች ይህን ቃል በዳዊት ጆሮ ተናገሩ፤ ዳዊትም፥ “እኔ የተዋረድሁና ክብር የሌለኝ ሰው ስሆን ለንጉሥ አማች እሆን ዘንድ ለእናንተ ትንሽ ነገር ይመስላችኋልን?” አለ።