አሁንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእግዚአብሔርን ነገር ለምን አቃለልህ? ኬጤያዊውን ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፤ ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል፤ እርሱንም በአሞን ልጆች ሰይፍ ገድለሃል።
ዘኍል 15:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ቃል ስለናቀ፥ ትእዛዙንም ስለ ሰበረ፥ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ ኀጢአቱ በራሱ ላይ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ናቀ፣ ትእዛዞቹንም ስለ ጣሰ ያ ሰው በርግጥ ተለይቶ መጥፋት አለበት፤ ጥፋቱ የራሱ ነው።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታን ቃል ስለ ናቀ፥ ትእዛዙንም ስላፈረሰ፥ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ በደሉ በራሱ ላይ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሚደርስበት እግዚአብሔር የተናገረውን ችላ ስላለና ከትእዛዞቹም አንዱን ሆን ብሎ ስለ ጣሰ ነው፤ ስለዚህ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ ኀላፊነቱ የራሱ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ናቀ፥ ትእዛዙንም ስለ ሰበረ፥ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ ኃጢአቱ በራሱ ላይ ነው። |
አሁንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእግዚአብሔርን ነገር ለምን አቃለልህ? ኬጤያዊውን ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፤ ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል፤ እርሱንም በአሞን ልጆች ሰይፍ ገድለሃል።
የእግዚአብሔርን ሥራ የሚያቃልለውን እርሱ ያቃልለዋል፥ ትእዛዙን የሚሰማ ግን በእርሱ በሕይወት ይኖራል። ለውሸተኛ ልጅ ምንም ደግነት የለም፥ ለብልህ አገልጋይ ግን ሥራው መልካም ይሆናል። መንገዱም ይቃናል።
ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፥ “ይህችን ቃል አቃልላችኋልና፥ በሐሰትና በጠማማነት ተስፋ አድርጋችኋልና፥ አጕረምርማችኋልምና፥ በዚህም ቃል ታምናችኋልና፤
እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም ስለ ኀጢአታችን ለሞት አሳልፎ ሰጠው።
ኀጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች፤ ልጅ የአባቱን ኀጢአት አይሸከምም፤ አባትም የልጁን ኀጢአት አይሸከምም፤ የጻድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆናል፤ የኀጢአተኛውም ኀጢአት በራሱ ላይ ይሆናል።
ሥርዐቴንም ብትንቁ፥ ትእዛዛቴንም ሁሉ እንዳታደርጉ፥ ቃል ኪዳኔንም እንድታፈርሱ ሰውነታችሁ ፍርዴን ብትሰለች፥
ምድርም ከእነርሱ መጥፋት የተነሣ ባዶ ትቀራለች፤ እነርሱም ሳይኖሩ በተፈታችበት ዘመን ዕረፍት ታደርጋለች፤ ፍርዴንም ስለ ናቁ፥ ነፍሳቸውም ሥርዐቴን ስለ ተጸየፈች የኀጢአታቸውን ቅጣት ይሸከማሉ።
“አንድ ሰው ቢበድል፥ የሚያምለውንም ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ፥ ወይም ዐውቆ እንደ ሆነ ያነን ባይናገር በደሉን ይሸከማል፤
ነገር ግን ንጹሕ የሆነ ሰው በመንገድም ላይ ያልሆነ ፋሲካን ባያደርግ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል፤ የእግዚአብሔርን ቍርባን በጊዜው አላቀረበምና ያ ሰው ኀጢአቱን ይሸከማል።
ማናቸውም ሰው ቢኰራ፥ በአምላክህ እግዚአብሔር ስም ለማገልገል የሚቆመውን ካህኑን ወይም በዚያ ወራት ያለውን ፈራጁን ባይሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእስራኤልም ዘንድ ክፉውን አስወግዱ፤