La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 14:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በእኔ ላይ በተ​ሰ​በ​ሰበ በዚህ ክፉ ማኅ​በር ሁሉ ላይ እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብዬ ተና​ገ​ርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያል​ቃሉ፤ በዚ​ያም ይሞ​ታሉ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አንድ ሆኖ በተነሣብኝ በዚህ ክፉ ማኅበረ ሰብ ሁሉ ላይ እነዚህን ነገሮች አደርጋለሁ፤ መጨረሻቸው በዚሁ ምድረ በዳ ይሆናል፤ እዚሁም ይሞታሉ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔ ጌታ፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ በእውነት እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፥ በዚያም ይሞታሉ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በእኔ ላይ አድመው በተነሡብኝ በእነዚህ ዐመፀኞች ላይ ይህን ሁሉ አደርግባቸዋለሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ የሁሉም መጨረሻ ይሆናል፤ ሁሉም ይሞታሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔ እግዚአብሔር፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፥ በዚያም ይሞታሉ።

Ver Capítulo



ዘኍል 14:35
10 Referencias Cruzadas  

ራስ​ህን ጠብቅ፤ ስማው፤ እን​ቢም አት​በ​ለው፤ ስሜ በእ​ርሱ ስለ ሆነ ይቅር አይ​ል​ምና።


በግ​ብፅ ምድረ በዳ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ጋር እንደ ተፋ​ረ​ድሁ እን​ዲሁ ከእ​ና​ንተ ጋር እፋ​ረ​ዳ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰው የሚ​ታ​ለል አይ​ደ​ለም። እንደ ሰው ልጅም የሚ​ዛ​ት​በት አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ያለ​ውን አያ​ደ​ር​ገ​ው​ምን? አይ​ና​ገ​ረ​ው​ምን? አይ​ፈ​ጽ​መ​ው​ምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ፥ “በእ​ው​ነት በም​ድረ በዳ ይሞ​ታሉ” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና። ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ፥ ከነ​ዌም ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው ስንኳ አል​ቀ​ረም።


እነ​ር​ሱን ያገ​ኛ​ቸው ይህ ሁሉ ነገር በኋላ ዘመን ለም​ን​ነ​ሣው ለእኛ ትም​ህ​ር​ትና ምክር ሊሆ​ነን ምሳሌ ሆኖ ተጻፈ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከእ​ነ​ርሱ በሁ​ሉም ደስ አላ​ለ​ውም፤ ብዙ​ዎቹ በም​ድረ በዳ ወድ​ቀ​ዋ​ልና።


አላ​መ​ኑ​ምና፥ ለመ​ግ​ባት እን​ዳ​ል​ቻሉ እነሆ፥ እና​ያ​ለን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ለእኛ ይሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር እን​ደ​ማ​ያ​ሳ​ያ​ቸው የማ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ከግ​ብፅ የወጡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ያል​ሰሙ፥ እነ​ዚያ ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አርባ ዓመት በመ​ድ​በራ ምድረ በዳ ይዞሩ ነበር።