Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 14:35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አንድ ሆኖ በተነሣብኝ በዚህ ክፉ ማኅበረ ሰብ ሁሉ ላይ እነዚህን ነገሮች አደርጋለሁ፤ መጨረሻቸው በዚሁ ምድረ በዳ ይሆናል፤ እዚሁም ይሞታሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 እኔ ጌታ፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ በእውነት እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፥ በዚያም ይሞታሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 በእኔ ላይ አድመው በተነሡብኝ በእነዚህ ዐመፀኞች ላይ ይህን ሁሉ አደርግባቸዋለሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ የሁሉም መጨረሻ ይሆናል፤ ሁሉም ይሞታሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በእኔ ላይ በተ​ሰ​በ​ሰበ በዚህ ክፉ ማኅ​በር ሁሉ ላይ እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብዬ ተና​ገ​ርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያል​ቃሉ፤ በዚ​ያም ይሞ​ታሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 እኔ እግዚአብሔር፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፥ በዚያም ይሞታሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 14:35
10 Referencias Cruzadas  

ይዋሽ ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፤ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም፤ ተናግሮ አያደርገውምን? ተስፋ ሰጥቶስ አይፈጽመውምን?


ይሁን እንጂ እግዚአብሔር በብዙዎቹ ደስ ስላልተሠኘ በበረሓ ወድቀው ቀሩ።


እንግዲህ ሊገቡ ያልቻሉት ካለማመናቸው የተነሣ እንደ ሆነ እንረዳለን።


ምክንያቱም በርግጥ በምድረ በዳ እንደሚሞቱ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ነግሯቸው ነበር፤ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ የተረፈ ማንም ሰው አልነበረም።


ይህ ሁሉ ምሳሌ ይሆን ዘንድ በእነርሱ ላይ ደረሰ፤ የዘመናት ፍጻሜ የደረሰብንን እኛን ለማስጠንቀቅም ተጻፈ።


ስለዚህ ዘመናቸውን በከንቱ፣ ዕድሜያቸውንም በድንጋጤ ጨረሰ።


በጥንቃቄ ተከተለው፤ የሚናገረውንም ልብ ብለህ ስማው፤ አታምፅበት። ስሜ በርሱ ላይ ነውና ዐመፅህን ይቅር አይልም።


ግብጽን ለቅቀው በወጡ ጊዜ መሣሪያ ለመያዝ የደረሱ ወንዶች ሁሉ ለእግዚአብሔር ስላልታዘዙ፣ እነርሱ ሞተው እስኪያልቁ ድረስ፣ እስራኤላውያን በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይንከራተቱ ነበር። እግዚአብሔር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው ቃል የገባላቸውን ያችን ማርና ወተት የምታፈስስ ምድር እንደማያዩአት ምሏልና።


በግብጽ ምድረ በዳ ከአባቶቻችሁ ጋራ እንደ ተፋረድሁ፣ ከእናንተም ጋራ እፋረዳለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios