ዘኍል 13:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወጡም፤ ምድሪቱንም ከጺን ምድረ በዳ በኤማት ዳር እስካለችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ወጥተው ከጺን ምድረ በዳ አንሥቶ በሌቦ ሐማት በኩል እስከ ረአብ ድረስ ዘልቀው ምድሪቱን አጠኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወጡም ምድሪቱንም ከጺን ምድረ በዳ ለሌብ ሐማት ቅርብ እስከሆነችው እስከ ረዓብ ድረስ ሰለሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሰዎቹ ወደ ሰሜን ሄዱ፤ በአገሪቱም ከሚገኘው ከጺን ምድረ በዳ ጀምረው ለሐማት መተላለፊያ ቅርብ እስከሆነው ረሖብ ድረስ አጠኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወጡም ምድሪቱንም ከጺን ምድረ በዳ በሐማት ዳር እስካለችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ። |
“ስለ ደማስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰምተዋልና ሐማትና አርፋድ አፈሩ፤ ቀለጡም፤ እንደ ባሕርም ተነዋወጡ፤ ያርፉም ዘንድ አይችሉም።
ንጉሡንም ይዘው የባቢሎን ንጉሥ ወዳለባት በኤማት ምድር ወዳለችው ወደ ዴብላታ አመጡት፤ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ።
ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደማስቆ ድንበርና በሐማት ድንበር መካከል ያለው ሲብራይም፥ በሐውራን ድንበር አጠገብ ያለው ሐጸርሃቲኮን።
የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ወደ ካልኔ ተሻግራችሁ ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ኤማትራባ እለፉ፤ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፤ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይበረታሉ፤ ድንበራቸውም ከድንበራቸው ይሰፋልና።
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፤ ተቀበረችም።
እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አላከበራችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የክርክር ውኃ ነው።”
ከጋስዮንጋቤርም ተጕዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከጺን ምድረ በዳም ተጕዘው በፋራን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ይህችም ቃዴስ ናት።
በእስራኤል ልጆች መካከል በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ባለው በክርክር ውኃ ለቃሌ አልታዘዛችሁምና፥ በእስራኤልም ልጆች መካከል አልቀደሳችሁኝምና፥
በፍልስጥኤም ያለው የጌባላውያን ምድር ሁሉ፥ በምሥራቅም በኩል ከአርሞንዔም ተራራ በታች ካለችው ጌልገላ ጀምሮ እስከ ኤማት መግቢያ ድረስ ያለችው ሊባኖስ ሁሉ፥
የሚታደግም አልነበረም፤ ከሲዶና ርቀው ነበርና፥ እነርሱም ከሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙነት አልነበራቸውምና። እርስዋም በቤትሮአብ አጠገብ ባለች ሸለቆ ውስጥ ነበረች፤ ከተማዪቱንም ሠርተው ተቀመጡባት።