ዘኍል 11:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፥ “ለምን በአገልጋይህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስን አላገኘሁም? ለምንስ የዚህን ሁሉ ሕዝብ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል ጠየቀው፤ “እንዲህ ያለውን መከራ በባሪያህ ላይ ለምን አመጣህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስ አላገኘሁም? የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም የጫንህብኝስ ምን አስቀይሜህ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ጌታን እንዲህ አለው፦ “ለምን በባርያህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስ አላገኘሁም? ለምንስ የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፦ “ይህን ከባድ ነገር በእኔ በአገልጋይህ ላይ ስለምን አመጣህብኝ? ለምንስ በፊትህ ሞገስን አላገኘሁም? የዚህን ሁሉ ሕዝብስ ከባድ ኀላፊነት ለምን በእኔ ላይ ጫንከው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፦ ለምን በባሪያህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስ አላገኘሁም? ለምንስ የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ? |
የሚምረኝ፥ መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና አዳኜ፤ መታመኛዬም፤ እርሱን ታመንሁ፤ ሕዝቡንም ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ።
ሙሴም፦ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እንዲህም አለ፥ “ለዚህ ሕዝብ ምን ላድርግ? በድንጋይ ሊወግሩኝ ጥቂት ቀርቶአቸዋልና።”
እናቴ ሆይ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን እኔን ወልደሽኛልና ወዮልኝ! ለማንም አልጠቀምሁም፤ ማንም እኔን አልጠቀመኝም፤ ከሚረግሙኝም የተነሣ ኀይሌ አለቀ።
የሚያሳዝኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበረታሉ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ አልሽርም አለ? እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃም ሆነብኝ።
እናንተም፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፣ ትእዛዙንስ በመጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል?
ሙሴም እያንዳንዳቸው በየወገናቸው በድንኳኑ ደጃፍ፥ ሲያለቅሱ ሰማ፤ እግዚአብሔርም እጅግ ተቈጣ፤ ነገሩም በሙሴ ፊት ክፉ ሆነ።
እንዲህስ ከምታደርግብኝ፥ በፊትህ ይቅርታን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ በእኔ ላይ የሚሆነውን መከራ እንዳላይ፥ እባክህ፥ ፈጽሞ ግደለኝ።”