Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 5:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለ​ሰና፥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ​ምን ይህን ሕዝብ አስ​ከ​ፋህ? ስለ ምንስ ላክ​ኸኝ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ፣ “አቤቱ ጌታ ሆይ፤ በዚህ ሕዝብ ላይ መከራ ያመጣኸው ለምንድን ነው? የላክኸኝ ለዚሁ ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሙሴም ወደ ጌታ ተመለሰና፦ “ጌታ ሆይ፥ ለምን ይህን ሕዝብ አስከፋህ? ለምንስ ላክኸኝ?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ሙሴም እንደገና ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ እንዲህ አለ፤ “አምላክ ሆይ! በዚህ ሕዝብ ላይ ይህን ያኽል መከራ የምታደርስበት ስለምንድነው? እንዲህ ከሆነ እኔንስ ወደዚህ ስለምን ላክኸኝ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተመለሰና፦ “ጌታ ሆይ! ስለ ምን ይህን ሕዝብ አስከፋህ? ስለ ምንስ ላክኸኝ?

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 5:22
12 Referencias Cruzadas  

አቤቱ! አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ እኔም ተታ​ለ​ልሁ፤ ከእ​ኔም በረ​ታህ አሸ​ነ​ፍ​ህም፤ ቀኑን ሁሉ መሳ​ቂያ ሆኛ​ለሁ፤ ሁሉም ያፌ​ዙ​ብ​ኛል።


ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፣ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፣ እርሱ አይዘገይም።


ኤል​ያ​ስም፥ “ሁሉን ለሚ​ገዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ቀን​ቻ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቃል ኪዳ​ን​ህን ትተ​ዋ​ልና፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ ነቢ​ያ​ት​ህ​ንም በሰ​ይፍ ገድ​ለ​ዋ​ልና፤ እኔም ብቻ​ዬን ቀር​ቻ​ለሁ ነፍ​ሴ​ንም ሊወ​ስ​ዱ​አት ይሻሉ” አለ።


እር​ሱም አንድ ቀን የሚ​ያ​ህል መን​ገድ በም​ድረ በዳ ሄደ፤ መጥ​ቶም ከደ​ድሆ ዛፍ በታች ተቀ​መ​ጠና፦ ይበ​ቃ​ኛል፤ አሁ​ንም አቤቱ! እኔ ከአ​ባ​ቶቼ አል​በ​ል​ጥ​ምና ነፍ​ሴን ውሰድ” ብሎ እን​ዲ​ሞት ለመነ።


ስለ ወን​ዶ​ችና ስለ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም የሕ​ዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበ​ርና ሕዝቡ ሊወ​ግ​ሩት ስለ ተና​ገሩ ዳዊት እጅግ ተጨ​ነቀ፤ ዳዊት ግን በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን አጽ​ናና።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ለምን በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ላይ ክፉ አደ​ረ​ግህ? ለም​ንስ በፊ​ትህ ሞገ​ስን አላ​ገ​ኘ​ሁም? ለም​ንስ የዚ​ህን ሁሉ ሕዝብ ሸክም በእኔ ላይ አደ​ረ​ግህ?


ሙሴም፦ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ለዚህ ሕዝብ ምን ላድ​ርግ? በድ​ን​ጋይ ሊወ​ግ​ሩኝ ጥቂት ቀር​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።”


አቤቱ! ከአ​ንተ ጋር በተ​ም​ዋ​ገ​ትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ጋር ስለ ፍርድ ልና​ገር። የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች መን​ገድ ስለ ምን ይቀ​ናል? በደ​ል​ንስ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላ​ቸ​ዋል?


እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ወዮ! አንተ ሰይፍ እስከ ሰው​ነ​ታ​ቸው ድረስ እስ​ክ​ት​ደ​ርስ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል” ብለህ ይህን ሕዝ​ብና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እጅግ አታ​ለ​ልህ አልሁ።


ኢያ​ሱም አለ፥ “ወዮ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን እጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠን፥ ታጠ​ፋ​ንም ዘንድ አገ​ል​ጋ​ይህ ይህን ሕዝብ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ለምን አሻ​ገረ? በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ተቀ​ም​ጠን በኖ​ርን ነበር እኮ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios