ደክሞና እጁ ዝሎ ሳለ እወድቅበታለሁ፤ አስፈራውማለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ይሸሻል፤ ንጉሡንም ብቻውን እገድለዋለሁ፤
ነህምያ 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደላቸውንም አትክደን፤ ኀጢአታቸውም ከፊትህ አይደምሰስ፤ በሠራተኞች ፊት አስቈጥተውሃልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈረሰውን በሚሠሩት ፊት የስድብ ናዳ አውርደዋልና በደላቸውን ይቅር አትበል፤ ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አታጥፋው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠላቶቻችንም፦ “በመካከላቸው እስክንገባና እስክንገድላቸው ድረስ፥ ሥራቸውንም እስክናስተጓጉል ድረስ አያውቁም፥ አያዩምም” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለሚያደርጉት ክፉ ነገር ምሕረት አታድርግላቸው፤ የፈረሰውን በመሥራታችን በስድብ አዋርደውናልና በደላቸውን አትርሳ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደላቸውንም አትክደን፥ ኃጢአታቸውም ከፊትህ አይደምሰስ፥ በሠራተኞች ፊት አስቆጥተውሃልና። |
ደክሞና እጁ ዝሎ ሳለ እወድቅበታለሁ፤ አስፈራውማለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ይሸሻል፤ ንጉሡንም ብቻውን እገድለዋለሁ፤
አድርገህልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ፥ በጻድቃንህም ዘንድ መልካም ነውና ምሕረትህን ተስፋ አደርጋለሁ።
አንተ ግን አቤቱ! ይገድሉኝ ዘንድ በላዬ የመከሩትን ምክር ሁሉ ታውቃለህ፤ በደላቸውንም ይቅር አትበል፤ ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤ በፊትህም ይውደቁ፤ በቍጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።”
ታው። ልቅሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና፥ ክፋታቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድረስ፥ ስለ ኀጢአቴ ሁሉ እኔን እንደ ቃረምኸኝ እነርሱን ቃርማቸው።