ሚክያስ 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቴ ሆይ፤ በእኔ ላይ በደረሰው ደስ አይበልሽ! ብወድቅም እንኳ እነሣለሁ፤ በጨለማ ብቀመጥ እንኳ፣ እግዚአብሔር ብርሃኔ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠላቴ ሆይ በእኔ ደስ አይበልሽ፤ ብወድቅ እነሣለሁና፤ በጨለማ ብቀመጥ ጌታ ብርሃኔ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቴ ሆይ! እኔ ብወድቅም እንኳ እንደገና እነሣለሁና በእኔ ደስ አይበልህ፤ አሁን በጨለማ ውስጥ ብሆንም እግዚአብሔር ያበራልኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ። |
አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቸልም አትበለኝ። ቸል ብትለኝ ግን ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እሆናለሁ።
የተጋዙትንም፦ ውጡ፤ በጨለማም የተቀመጡትን፦ ተገለጡ፤ ትል ዘንድ።” በመንገድም ሁሉ ላይ ይሰማራሉ፤ ማሰማሪያቸውም በጥርጊያ ጎዳና ሁሉ ላይ ይሆናል።
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ማን ነው? የባሪያውንም ቃል ይስማ፤ በጨለማም የምትሄዱ፥ ብርሃንም የሌላችሁ በእግዚአብሔር ስም ታመኑ፤ በእግዚአብሔርም ተደገፉ፤
እስራኤል ለአንተ መሳቂያ አልሆነምን? ወይስ በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን? ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ራስህን ትነቀንቃለህ።
“ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ብሎአችኋልና፥ ሐሤትንም አድርጋችኋልና፥ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ተቀናጥታችኋልና፥ እንደ ብርቱዎችም በሬዎች ቷጋላችሁና፤
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእጆችህ አጨብጭበሃልና፥ በእግሮችህም አሸብሽበሃልና፥ ሰውነትህም በእስራኤል ምድር ላይ ደስ ብሎአታልና፤
የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እንዳለህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ፤ የሴይር ተራራ ሆይ! አንተና መላው ኤዶምያስ ባድማ ትሆናላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።”
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንአቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤
“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ቤት አነሣለሁ፤ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፤ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤
በጠላት ቀን ወንድምህን ዝቅ አድርገህ ትመለከተው ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን በይሁዳ ልጆች ላይ ደስ ይልህ ዘንድ፥ በጭንቀታቸውም ቀን በትዕቢት ትናገር ዘንድ ባልተገባህ ነበር።
የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ፥ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ፥ በዚያም ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።
በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፣ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፣ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል።
ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝኑማላችሁ፤ ዓለምም ደስ ይለዋል፤ እናንተ ግን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።
ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ፥ “የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃንን ያገኛል እንጂ በጨለማ ውስጥ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው።
ይኸውም ዐይናቸውን ትከፍትላቸው ዘንድ፥ ከጨለማም ወደ ብርሃን፥ ሰይጣንን ከማምለክም ወደ እግዚአብሔር ትመልሳቸው ዘንድ፥ ኀጢአታቸውም ይሰረይላቸው ዘንድ፥ በስሜም በማመን ከቅዱሳን ጋር አንድነትን ያገኙ ዘንድ ነው።’
በጨለማ ውስጥ “ብርሃን ይብራ” ያለ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የክብሩን ዕውቀት ብርሃን በልባችን አብርቶልናልና።
ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።