ሚክያስ 2:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብ ሆይ፥ ሁልንተናህን ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልንም ቅሬታ ፈጽሞ አከማቻለሁ፥ እንደ ባሶራ በጎችና እንደ መንጋ በማሰማርያቸው ውስጥ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፥ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ያዕቆብ ሆይ፤ በርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ፤ የእስራኤልንም ትሩፍ በአንድነት አመጣለሁ፤ በጕረኖ ውስጥ እንዳሉ በጎች በመሰማሪያ ላይ እንዳለ መንጋ በአንድነት እሰበስባቸዋለሁ፤ ቦታውም በሕዝብ ይሞላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብ ሆይ፥ ሁላችሁንም ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልን ትሩፍ በአንድ ላይ እሰበስባለሁ፤ በጋጣ ውስጥ እንዳሉ በጎች፥ በማሰማርያው ውስጥ እንዳለ መንጋ አደርገዋለሁ፤ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል ሕዝብ! በጎች በበረት፥ የበግ መንጋም በማሰማሪያ ቦታ እንደሚሰበሰብ በእርግጥ ከእስራኤል ሕዝብ የተረፉትን በአንድነት እሰበስባለሁ፤ ምድሪቱም በሕዝብ የተሞላች ትሆናለች” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብ ሆይ፥ ሁልንተናህን ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልንም ቅሬታ ፈጽሞ አከማቻለሁ፥ እንደ ባሶራ በጎችና እንደ መንጋ በማሰማርያቸው ውስጥ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፥ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ። |
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከባቢሎንና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላሜጤን፥ ከምሥራቅና ከምዕራብ ለቀሩት ለሕዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ዐጥር ያጥራል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፤ በበግ ስብ፥ በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ስብ ወፍራለች።
የተማረኩ እንደ በሬዎች ይሰማራሉ፤ የተረሱትም ምግባቸውን ሲፈልጉ እንደ በግ ጠቦቶች በማሰማርያቸው ይሰማራሉ።
የሕዝቤን ቅሬታ ከበተንኋቸው ምድር ሁሉ ወደ መሰማሪያቸው ሰብስቤ እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ይበዛሉ፤ ይባዛሉም።
በዚያም ዘመን የይሁዳ ቤት ወደ እስራኤል ቤት ይሄዳል፤ በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።
ከአሕዛብም ዘንድ አወጣቸዋለሁ፤ ከሀገሮችም ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ገዛ ሀገራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ፥ በፈሳሾችም አጠገብ፥ በምድርም ላይ ሰዎች በሚኖሩባት ስፍራ ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደርግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል፤ ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።
አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የእስራኤልን ልጆች ከገቡባቸው ከአሕዛብ መካከል እወስዳለሁ፤ ከስፍራም ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ እስራኤልም ምድር አመጣቸዋለሁ፤
የይሁዳ ልጆችና የእስራኤል ልጆች በአንድነት ይሰበሰባሉ፤ ለእነርሱም አንድ አለቃ ይሾማሉ፤ ከምድሪቱም ይወጣሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።
ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፥ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጥተዋል፥ ንጉሣቸውም በፊታቸው አልፎአል፥ እግዚአብሔርም በራሳቸው ላይ ነው።
አንተም የመንጋ ግንብ ሆይ፥ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ፥ ወደ አንተ ትመጣለች፥ የቀደመችው ግዛት፥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ትደርሳለች።
የያዕቆብም ቅሬታ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውንም እንደማይጠብቅ፥ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ይሆናል።
በዱር አራዊትም መካከል እንዳለ አንበሳ፥ በበጎች መንጋም መካከል አልፎ እንደሚረግጥ፥ የሚታደግም ሳይኖር እንደሚነጥቅ እንደ አንበሳ ደቦል፥ እንዲሁ የያዕቆብ ቅሬታ በአሕዛብና በብዙ ወገኖች መካከል ይሆናል።
በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።
በዚያ ዘመን አስገባችኋለሁ፥ በዚያም ዘመን እሰበስባችኋለሁ፣ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር አሕዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።