የከሓናም ልጅ ሴዴቅያስ ቀረበ፤ ሚክያስንም ጕንጩን በጥፊ መታውና፥ “ምን ዓይነት የእግዚአብሔር መንፈስ ነው የተናገረህ?” አለው።
ማቴዎስ 26:67 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ በፊቱ ተፉበት፤ ጐሰሙትም፤ ሌሎችም በጥፊ መትተው “ክርስቶስ ሆይ! በጥፊ የመታህ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ፊቱ ላይ እየተፉ በጡጫ መቱት፤ ሌሎቹም በጥፊ እየመቱት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ፊቱ ላይ ተፉበት፥ መቱት፥ በጥፊም መቱት አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ምራቃቸውን ተፉበት፤ ጎሸሙት፤ በጥፊም እየመቱት፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ በፊቱ ተፉበት፤ ጕኦሰሙትም፥ ሌሎችም በጥፊ መትተው፦ ክርስቶስ ሆይ፥ በጥፊ የመታህ ማን ነው? |
የከሓናም ልጅ ሴዴቅያስ ቀረበ፤ ሚክያስንም ጕንጩን በጥፊ መታውና፥ “ምን ዓይነት የእግዚአብሔር መንፈስ ነው የተናገረህ?” አለው።
መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም።
ጳስኮርም ነቢዩን ኤርምያስን ገረፈው፤ በእግዚአብሔርም ቤት በነበረው በላይኛው በብንያም በር ባለው አዘቅት ውስጥ ጣለው።
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “አባቷ ምራቁን በፊቷ ቢተፋባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰፈር ውጭ ተዘግታ ትቀመጥ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ትመለስ” አለው።
ይህንም ባለጊዜ ከቆሙት ሎሌዎች አንዱ፥ “ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልስለታለህን?” ብሎ ጌታችን ኢየሱስን በጥፊ መታው።
ዋርሳዪቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል’ ስትል የአንድ እግሩን ጫማ ታውጣ፤ በፊቱም እንትፍ ትበልበት።
የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ፥ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።