ኤልያስም፦ ስምህ እስራኤል ይሆናል የሚል የእግዚአብሔር ቃል እንደ ደረሰለት እንደ እስራኤል ልጆች ነገድ ቍጥር ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን ወሰደ።
ማቴዎስ 19:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ በሚመጣው አዲስ ዓለም የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ እናንተም የተከተላችሁኝ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ላይ ተቀምጣችሁ፣ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ላይ ትፈርዳላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ስለተከተላችሁኝ በዳግም ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በዓሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ፥ በዓሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ላይም ትፈርዳላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ የሰው ልጅ በክብር ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት በአዲሱ ዓለም የእኔ ተከታዮች የሆናችሁ፥ እናንተም፥ በዐሥራ ሁለት ዙፋኑ ላይ ትቀመጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ። |
ኤልያስም፦ ስምህ እስራኤል ይሆናል የሚል የእግዚአብሔር ቃል እንደ ደረሰለት እንደ እስራኤል ልጆች ነገድ ቍጥር ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን ወሰደ።
በስድስቱም እርከኖች ላይ በዚህና በዚያ ዐሥራ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር፤ በመንግሥታት ሁሉ እንዲህ ያለ ሥራ አልተሠራም።
በዚህም በእግዚአብሔር ቤት ቅዳሴ መቶ ወይፈኖችና ሁለት መቶ አውራ በጎች፥ አራት መቶም የበግ ጠቦቶች አቀረቡ፤ ስለ ኀጢአትም መሥዋዕት እንደ እስራኤል ነገዶች ቍጥር ለእስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ።
እነርሱም ወደ ኤሎም መጡ፤ በዚያም ዐሥራ ሁለት የውኃ ምንጮችና ሰባ የዘንባባ ዛፎች ነበሩባት፤ በዚያም በውኃው አጠገብ ሰፈሩ።
ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ፤ ማለዳም ተነሣ፤ ከተራራውም በታች መሠዊያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለትም ድንጋዮችን ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ አቆመ።
የዕንቍም ድንጋዮች እንደ እስራኤል ልጆች ስሞች ዐሥራ ሁለት ይሆናሉ፤ በየስማቸውም ማኅተም አቀራረጽ ይቀረጹ፤ ስለ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶችም ይሁኑ።
“እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።
“የስንዴ ዱቄት ወስደህ ዐሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር፤ በእያንዳንዱ ኅብስት ውስጥ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ ይሁን።
እርሱም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርስዋም “እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ፤” አለችው።
እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እስከ ተናገረው የመደራጀት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባል።
ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ፤ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የዐሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የተቀዳጀች አንዲት ሴት ነበረች።
ዙፋኖችንም አየሁ፤ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ።
ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።
በዙፋኑ ዙሪያም ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።