Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 66:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “እኔ የም​ሠ​ራ​ቸው አዲስ ሰማ​ይና አዲስ ምድር በፊቴ ጸን​ተው እን​ደ​ሚ​ኖሩ፥ እን​ዲሁ ዘራ​ች​ሁና ስማ​ችሁ ጸን​ተው ይኖ​ራሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ የእናንተና የዘራችሁ ስም እንደዚሁ ጸንቶ ይኖራል” ይላል እግዚአብሔር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “የምፈጥራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በእኔ ጸንተው እንደሚኖሩ እንዲሁም ዘራችሁና ስማችሁ በእኔ ጸንተው ይኖራሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 66:22
19 Referencias Cruzadas  

ዘር​ህም እንደ አሸዋ የሆ​ድ​ህም ትው​ልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፤ አሁ​ንም ስምህ ከፊቴ ባል​ጠ​ፋና ባል​ፈ​ረሰ ነበር።


ቃሌን በአ​ፍሽ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ሰማ​ይን በዘ​ረ​ጋ​ሁ​በ​ትና ምድ​ርን በመ​ሠ​ረ​ት​ሁ​በት በእጄ ጥላ እጋ​ር​ድ​ሻ​ለሁ፤ ጽዮ​ን​ንም አንቺ ሕዝቤ ነሽ እላ​ታ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ር​ፋቱ ያነ​ጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብታ​ቀ​ርቡ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ረዥም ዕድሜ ያለ​ውን ዘር ታያ​ለች።


በቤ​ቴና በቅ​ጥሬ ውስጥ ከወ​ን​ዶ​ችና ከሴ​ቶች ልጆች ይልቅ የሚ​በ​ልጥ ስም የሚ​ያ​ስ​ጠራ ቦታን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የማ​ይ​ጠፋ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


“ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “በአ​ንተ ላይ ያለው መን​ፈሴ በአ​ፍ​ህም ውስጥ ያደ​ረ​ግ​ሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ከአ​ፍህ፥ ከዘ​ር​ህም አፍ፥ ከዘር ዘር​ህም አፍ አይ​ጠ​ፋም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅን የም​ወ​ድድ፥ ስር​ቆ​ት​ንና ቅሚ​ያን የም​ጠላ ነኝ፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም ለጻ​ድ​ቃን እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ዘራ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በወ​ገ​ኖች መካ​ከል የታ​ወቁ ይሆ​ናሉ፤ ያያ​ቸው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የባ​ረ​ካ​ቸው ዘር እንደ ሆኑ ያው​ቃል፤


“እነሆ፥ አዲስ ሰማ​ይና አዲስ ምድር ይሆ​ና​ልና፤ የቀ​ደ​ሙ​ትም አይ​ታ​ሰ​ቡም፤ ወደ ልብም አይ​ገ​ቡም።


ሌላ እን​ዲ​ቀ​መ​ጥ​በት አይ​ሠ​ሩም፤ ሌላም እን​ዲ​በ​ላው አይ​ተ​ክ​ሉም፤ የሕ​ዝቤ ዕድሜ እንደ ሕይ​ወት ዛፍ ዕድሜ ይሆ​ና​ልና፥ እኔም የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው በእ​ጃ​ቸው ሥራ ረዥም ዘመን ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


እነ​ርሱ ከእ​ነ​ል​ጆ​ቻ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩ​ካን ዘር ናቸ​ውና በከ​ንቱ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ ለር​ግ​ማ​ንም አይ​ወ​ል​ዱም።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ቀንና ሌሊት በወ​ራ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሆኑ የቀን ቃል ኪዳ​ኔ​ንና የሌ​ሊት ቃል ኪዳ​ኔን ማፍ​ረስ ብት​ችሉ፥


በዙ​ፋኑ ላይ የሚ​ነ​ግሥ ልጅ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ለት ከባ​ሪ​ያዬ ከዳ​ዊት ጋር፥ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈ​ር​ሳል።


በዚያ ዘመን አስገባችኋለሁ፥ በዚያም ዘመን እሰበስባችኋለሁ፣ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር አሕዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ነገር ግን ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን።


አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፤ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፤ ባሕርም ወደ ፊት የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos