Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕዝራ 6:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቅዳሴ መቶ ወይ​ፈ​ኖ​ችና ሁለት መቶ አውራ በጎች፥ አራት መቶም የበግ ጠቦ​ቶች አቀ​ረቡ፤ ስለ ኀጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ቍጥር ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየ​ሎች አቀ​ረቡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ለዚህ ለእግዚአብሔር ቤት ምረቃም አንድ መቶ ወይፈኖችን፣ ሁለት መቶ አውራ በጎችንና አራት መቶ ተባዕት ጠቦቶችን ሰጡ፤ ለመላው እስራኤል የኀጢአት መሥዋዕትም ዐሥራ ሁለት ተባዕት ፍየሎችን በእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ ልክ አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ለዚህ የእግዚአብሔር ቤት ምረቃ አንድ መቶ ወይፈኖች፥ ሁለት መቶ አውራ በጎች፥ አራት መቶ የበግ ጠቦቶችን፥ ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት እንደ እስራኤል ነገዶች ቍጥር ለእስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እነርሱም ሁሉ ለበዓሉ የሚሆኑትን አንድ መቶ ወይፈኖችን፥ ሁለት መቶ በጎችንና አራት መቶ ጠቦቶችን ለመሥዋዕት አቀረቡ፤ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆኑም ዐሥራ ሁለት ፍየሎችን በእያንዳንዱ ነገድ ስም አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በዚህም በእግዚአብሔር ቤት ቅዳሴ መቶ ወይፈኖችና ሁለት መቶ አውራ በጎች፥ አራት መቶም ጠቦቶች አቀረቡ፤ ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት እንደ እስራኤል ነገዶች ቍጥር ለእስራኤል ሁሉ አሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 6:17
17 Referencias Cruzadas  

ከም​ር​ኮም የወ​ጡት የም​ር​ኮ​ኞች ልጆች ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ስለ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይ​ፈ​ኖች፥ ዘጠና ስድ​ስ​ትም አውራ በጎች፥ ሰባ ሰባ​ትም ጠቦ​ቶች፥ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየ​ሎ​ችን አቀ​ረቡ። ይህ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነበረ።


በዚ​ያ​ችም ዕለት ንጉሡ ሰሎ​ሞን ሃያ ሁለት ሺህ በሬ​ዎ​ች​ንና መቶ ሃያ ሺህ በጎ​ችን ሠዋ። እን​ዲሁ ንጉ​ሡና ሕዝቡ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቅዳሴ አከ​በሩ።


ኤል​ያ​ስም፦ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይሆ​ናል የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ደረ​ሰ​ለት እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ቍጥር ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን ወሰደ።


ለእ​ር​ሱም የሠ​ራው ኀጢ​አት ቢታ​ወ​ቀ​ውና ንስሓ ቢገባ፥ ስለ ሠራው ኀጢ​አት ነውር የሌ​ለ​ባ​ትን እን​ስት ፍየል ለቍ​ር​ባኑ ያመ​ጣል።


የተ​ቀ​ባ​ውም ሊቀ ካህ​ናት በሕ​ዝቡ ላይ በደል እን​ዲ​ቈ​ጠ​ር​ባ​ቸው ኀጢ​አት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢ​አቱ ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ወይ​ፈን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​በ​ዋል።


ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፤ ዐሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት፤ በደጆቹም ዐሥራ ሁለት መላእክት ቆሙ የዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።


በመ​ን​ግ​ሥቴ በማ​ዕዴ ትበ​ሉና ትጠጡ ዘንድ፥ በወ​ን​በ​ሮ​ችም ተቀ​ም​ጣ​ችሁ በዐ​ሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ትፈ​ርዱ ዘንድ።”


ንጉ​ሡም ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መሥ​ዋ​ዕት ሠዉ።


ካህ​ና​ቱም አረ​ዱ​አ​ቸው፤ ንጉ​ሡም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ እን​ዲ​ደ​ረግ አዝዞ ነበ​ርና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ማስ​ተ​ስ​ረያ ያደ​ርጉ ዘንድ ደማ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አቀ​ረቡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios