ማቴዎስ 10:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ይዘው ለፍርድ ወደ ሸንጎ ያቀርቧችኋል፤ በምኵራቦቻቸውም ይገርፏችኋል፤ ስለዚህ ከእነርሱ ተጠንቀቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰዎች ተጠንቀቁ፥ ምክንያቱም ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኵራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ወደ ፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በየምኲራባቸውም ይገርፉአችኋል፤ ስለዚህ ከሰዎች ተጠንቀቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ |
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤
እኔ ግን እላችኋለሁ፤በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።
“እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኵራብም ትገረፋላችሁ፤ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።
ወደ አደባባይ ወደ ሹሞቹና ወደ ነገሥታቱ፥ ወደ መኳንንቱም በሚወስዱአችሁ ጊዜ የምትሉትንና የምትናገሩትን አታስቡ።
የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ጉባኤውን ሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው ብዙ ተአምራት ያደርጋል፤ ምን እናድርግ?
ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ደግሞም እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።
እኔም እንዲህ አልሁት፦ ‘ጌታዬ ሆይ፥ በአንተ የሚያምኑትን በየምኵራቦቻቸው ሳስራቸውና ስደበድባቸው የነበርሁ እኔ እንደ ሆንሁ እነርሱ ያውቃሉ።
በየምኵራቡ ሁሉ የማስገደጃ ማዘዣ አምጥቼ፥ በግድ የኢየሱስን ስም እንዲሰድቡ ዘወትር መከራ አጸናባቸው ነበር፤ ይልቁንም ወደ ሌሎች ከተማዎች እያሳደድሁ ከፋሁባቸው።
ምንአልባት በመንገድ የሚያገኘው ሰው ቢኖር ወንዶችንም ሴቶችንም እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች የሥልጣን ደብዳቤ ከሊቀ ካህናቱ ለመነ።