Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 17:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ያን​ጊ​ዜም ወን​ድ​ሞች ጳው​ሎ​ስን ሸኝ​ተው ወደ ባሕር አደ​ረ​ሱት፤ ሲላ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎስ ግን በዚ​ያው ቀሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በዚህ ጊዜ ወንድሞች ጳውሎስን ቶሎ ብለው ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሰደዱት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስ ግን እዚያው ቀሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በዚያን ጊዜም ወንድሞች ወዲያው ጳውሎስን እስከ ባሕር ድረስ ይሄድ ዘንድ ሰደዱት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስም በዚያው ቀሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በዚህ ጊዜ ወንድሞች በቶሎ ጳውሎስ ወደ ባሕሩ አጠገብ እንዲሄድ አደረጉት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስ ግን እዚያው በቤርያ ቀሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በዚያን ጊዜም ወንድሞቹ ወዲያው ጳውሎስን እስከ ባሕር ድረስ ይሄድ ዘንድ ሰደዱት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስም በዚያው ቀሩ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 17:14
16 Referencias Cruzadas  

ወን​ድ​ሞች ግን ጳው​ሎ​ስ​ንና ሲላ​ስን በሌ​ሊት ወደ ቤርያ ሸኙ​አ​ቸው፤ ወደ​ዚ​ያም በደ​ረሱ ጊዜ ወደ አይ​ሁድ ምኵ​ራብ ገቡ።


በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።


ወደ ደር​ቤ​ንና ወደ ልስ​ጥ​ራን ከተ​ማም ደረሰ፤ እነ​ሆም፥ በዚያ የአ​ን​ዲት ያመ​ነች አይ​ሁ​ዳ​ዊት ልጅ ጢሞ​ቴ​ዎስ የሚ​ባል አንድ ደቀ መዝ​ሙር ነበር፤ አባቱ ግን አረ​ማዊ ነበረ።


ወን​ድ​ሞ​ችም ይህን ባወቁ ጊዜ ወደ ቂሳ​ርያ አወ​ረ​ዱት፤ ከዚ​ያም ወደ ጠር​ሴስ ላኩት።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም በሌ​ሊት ወሰ​ዱት፤ በቅ​ር​ጫ​ትም አድ​ር​ገው በቅ​ጽሩ ድም​ድ​ማት ላይ አወ​ረ​ዱት።


ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤


ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና፤ በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም።


በዚ​ያም ሦስት ወር ተቀ​መጠ፤ ወደ ሶር​ያም በመ​ር​ከብ ለመ​ሄድ ዐስቦ ሳለ አይ​ሁድ ስለ ተማ​ከ​ሩ​በት ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሊመ​ለስ ቈረጠ።


ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ትም ሁለ​ቱን ጢሞ​ቴ​ዎ​ስ​ንና አር​ስ​ጦ​ስን ወደ መቄ​ዶ​ንያ ላከ፤ እርሱ ራሱ ጳው​ሎስ ግን ብዙ ቀን በእ​ስያ ተቀ​መጠ።


ከዚ​ህም በኋላ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሕዝ​ቡም ሁሉ ከጳ​ው​ሎ​ስና ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ አን​ጾ​ኪያ የሚ​ል​ኳ​ቸ​ውን ሰዎች ይመ​ርጡ ዘንድ ተስ​ማሙ፤ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸው መካ​ከ​ልም የተ​ማ​ሩ​ትን ሰዎች በር​ና​ባስ የተ​ባለ ይሁ​ዳ​ንና ሲላ​ስን መረጡ።


እር​ስ​ዋም፥ “የሚ​ከ​ተ​ሉ​አ​ችሁ እን​ዳ​ያ​ገ​ኙ​አ​ችሁ ወደ ተራ​ራው ሂዱ፤ የሚ​ከ​ተ​ሉ​አ​ች​ሁም እስ​ከ​ሚ​መ​ለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰ​ው​ራ​ችሁ ተቀ​መጡ፤ በኋ​ላም መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ” አለ​ቻ​ቸው።


ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮስ ተነ​ሣና በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቆመ፤ መቶ ሃያ ያህል ሰዎ​ችም በዚያ ሳሉ እን​ዲህ አላ​ቸው።


ከእ​ነ​ር​ሱና ከደ​ጋ​ጎች አረ​ማ​ው​ያ​ንም ብዙ ሰዎች፥ ከታ​ላ​ላ​ቆች ሴቶ​ችም ጥቂ​ቶች ያይ​ደሉ አም​ነው ከጳ​ው​ሎ​ስና ከሲ​ላስ ጋር ሆኑ።


በአ​ጧ​ቸ​ውም ጊዜ ኢያ​ሶ​ንን ጐተ​ቱት፤ በዚ​ያም የነ​በ​ሩ​ትን ጓደ​ኞች ጭምር ወደ ሹሞቹ ወሰ​ዱ​አ​ቸው፤ እየ​ጮ​ኹም እን​ዲህ ይሉ ነበር፥ “ዓለ​ምን የሚ​ያ​ው​ኳት እነ​ዚህ ናቸው፤ ወደ​ዚ​ህም መጥ​ተ​ዋል።


ጳው​ሎ​ስን የሸ​ኙት ሰዎ​ችም እስከ አቴና ከተማ ድረስ አብ​ረ​ውት መጥ​ተው ነበ​ርና ፈጥ​ነው ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ወደ ሲላ​ስና ወደ ጢሞ​ቴ​ዎስ ላካ​ቸው፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ሄዱ።


ሲላ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም ከመ​ቄ​ዶ​ንያ በወ​ረዱ ጊዜ ጳው​ሎስ፥ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ለአ​ይ​ሁድ እየ​መ​ሰ​ከረ ቃሉን በማ​ስ​ተ​ማር ይተጋ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios