ማርቆስ 15:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራሱንም በመቃ መቱት፤ ተፉበትም፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሱንም በበትር መቱት፤ ተፉበትም፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሱንም በበትር መቱት፤ ተፉበትም፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመቃ ራስ ራሱን ይመቱት ነበር፤ ምራቃቸውንም እንትፍ ይሉበት ነበር፤ በፊቱም በማላገጥ እየተንበረከኩ ይሰግዱለት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት። |
እነርሱም አሉት፥ “ባሪያህ ሽማግሌው አባታችን ደኅና ነው፤ ገና በሕይወት አለ።” ዮሴፍም አለ፥ “ሰውየው እግዚአብሔር የባረከው ነው።” ራሳቸውንም ዝቅ አድርገው ሰገዱለት።
እኔም ከእስራኤል ጕልበታቸውን ለበዓል ያላንበረከኩትን ሁሉ፥ በአፋቸውም ያልሳሙትን ሁሉ፥ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀራለሁ።”
ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፤ አትመለስምም፤ ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ በእግዚአብሔር ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።”
ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።”