Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 22:63 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

63 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይዘ​ውት የነ​በ​ሩት ሰዎ​ችም ይዘ​ባ​በ​ቱ​በ​ትና ይደ​በ​ድ​ቡት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

63 ኢየሱስን አስረው ይጠብቁት የነበሩት ሰዎችም ያፌዙበትና ይመቱት ጀመር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

63 ኢየሱስንም የያዙት ሰዎች ይቀልዱበትና ይደበድቡት ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

63 በዚያን ጊዜ ኢየሱስን ይዘውት የነበሩ ሰዎች በእርሱ ላይ ያፌዙበትና ይደበድቡትም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

63 ኢየሱስንም የያዙት ሰዎች ይዘብቱበትና ይደበድቡት ነበር፤

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 22:63
23 Referencias Cruzadas  

ይህ​ንም ባለ​ጊዜ ከቆ​ሙት ሎሌ​ዎች አንዱ፥ “ለሊቀ ካህ​ናቱ እን​ዲህ ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለ​ህን?” ብሎ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በጥፊ መታው።


ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤


የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።


የጭፍሮች ሴት ልጅ ሆይ፥ ጭፍሮችሽን አሁን ሰብስቢ፥ ከብቦ አስጨንቆናል፥ የእስራኤልን ፈራጅ ጕንጩን በበትር ይመታሉ።


መል​ኩም የተ​ናቀ፥ ከሰ​ውም ልጆች ሁሉ የተ​ዋ​ረደ፥ የተ​ገ​ረፈ ሰው፥ መከ​ራ​ንም የተ​ቀ​በለ ነው፤ ፊቱ​ንም መል​ሶ​አ​ልና አቃ​ለ​ሉት፥ አላ​ከ​በ​ሩ​ት​ምም።


ፊቱ ከሰ​ዎች ሁሉ ይልቅ፥ መል​ኩም ከሰ​ዎች ልጆች ይልቅ ያለ ክብር ነውና ብዙ ሰዎች ስለ እርሱ ያደ​ን​ቃሉ፤


ታዳ​ጊህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕይ​ወ​ቱን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ትን፥ በአ​ሕ​ዛብ የተ​ጠ​ላ​ውን የአ​ለ​ቆ​ችን ባርያ ቀድ​ሱት፤ ነገ​ሥ​ታት ያዩ​ታል፤ አለ​ቆ​ችም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብለው ተነ​ሥ​ተው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መር​ጨ​ሃ​ለ​ሁና።”


ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ውጭ ወጥቶ መራራ ልቅ​ሶን አለ​ቀሰ።


ሊቀ ካህ​ና​ቱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፦ ስለ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱና ስለ ትም​ህ​ርቱ ጠየ​ቀው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios