ማርቆስ 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጲላጦስም የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጲላጦስም ሕዝቡን ደስ ለማሠኘት ሲል በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጲላጦስም ሕዝቡን ደስ ለማሰኘት ሲል በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጲላጦስ ሰዎቹን ደስ ለማሰኘት ብሎ በርባንን ፈቶ ለቀቀላቸው፤ ኢየሱስን ግን አስገረፈውና እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጲላጦስም የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ። |
ሁለት ዓመትም ካለፈ በኋላ፥ ፊልክስ ተሻረና ጶርቅዮስ ፊስጦስ የሚባል ሌላ ሀገረ ገዢ በእርሱ ቦታ መጣ፤ ፊልክስም በግልጥ ለአይሁድ ሊያዳላ ወደደ፤ ስለዚህም ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው።
ፊስጦስ ግን አይሁድ እንዲያመሰግኑት ወዶ ጳውሎስን፥ “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተህ ስለዚህ ነገር በዚያ ከእኔ ዘንድ ልትከራከር ትሻለህን?” አለው።