ሉቃስ 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም ፈሩ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ እንዲህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነሣልን፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጐብኝቶአልና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም በፍርሀት ተውጠው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ፣ “ታላቅ ነቢይ በመካከላችን ተነሥቷል፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን ጐብኝቷል” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉንም ፍርሃት ያዛቸው፤ እግዚአብሔርንም እንዲህ እያሉ አመሰገኑ፦ “ታላቅ ነቢይ በእኛ መካከል ተነሥቶአል!” “እግዚአብሔርም ሕዝቡን ጐብኝቶአል!” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉንም ፍርሀት ይዞአቸው፥ “ታላቅ ነቢይ ከመካከላችን ተነሥቶአል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊያድን መጥቶአል፤” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉንም ፍርሃት ያዛቸውና፦ ታላቅ ነቢይ በእኛ መካከል ተነሥቶአል፥ ደግሞ፦ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጐበኘ እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። |
ሕዝቡም አመኑ፤ ደስም አላቸው፤ እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች ጐብኝቶአልና፤ ጭንቀታቸውንም አይቶአልና፤ ሕዝቡም ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ።
ይህችም ከተማ እኔ የምሠራላቸውን በጎነት ሁሉ በሚሰሙ፥ እኔም ስላመጣሁላቸው በጎነትና ሰላም ሁሉ በሚፈሩና በሚደነግጡ አሕዛብ ሁሉ ፊት ለደስታ፥ ለክብርና ለገናንነት ትሆናለች።”
አንቺን ይጥሉሻል፤ ልጆችሽንም ከአንቺ ጋር ይጥሉአቸዋል፤ ድንጋይንም በደንጋይ ላይ አይተዉልሽም፤ የይቅርታሽን ዘመን አላወቅሽምና።”
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ይህ ምንድነው?” አላቸው፤ እነርሱም እንዲህ አሉት፥ “በእግዚአብሔር ፊትና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በቃሉና በሥራው ብርቱ ነቢይና እውነተኛ ሰው ስለነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፥
ስምዖን ጴጥሮስም ይህን አይቶ ከጌታችን ከኢየሱስ እግር በታች ሰገደና፥ “እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።
የጠራው ፈሪሳዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እንዴትስ እንደ ነበረች ባላወቀም ነበርን? ኀጢአተኛ ናትና።”
በጌርጌሴኖንም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ከእነርሱ ዘንድ እንዲሄድላቸው ማለዱት፤ ጽኑ ፍርሀት ይዞአቸዋልና፤ ጌታችን ኢየሱስም በታንኳ ሆኖ ተመለሰ።
እነርሱም መልሰው፥ “መጥምቁ ዮሐንስ ነው የሚሉህ አሉ፤ ኤልያስ ነው የሚሉህም አሉ፤ ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል የሚሉህም አሉ” አሉት።
“እንኪያ አንተ ማነህ? አንተ ኤልያስ ነህን?” ብለው ጠየቁት፤ “አይደለሁም” አለ፤ “እንኪያ አንተ ነቢዩ ነህን?” አሉት፤ “አይደለሁም” አለ።
“እንኪያስ ክርስቶስን ካልሆንህ፥ ኤልያስንም ካልሆንህ፥ ነቢይንም ካልሆንህ ለምን ታጠምቃለህ?” ብለው ጠየቁት።
ዳግመኛም ዕዉሩን፥ “አንተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ? ዐይኖችህን ከፍቶልሃልና” አሉት፤ እርሱም፥ “ነቢይ ነው” አላቸው።
ለእስራኤልም ልጆች፦ ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋልና እርሱን ስሙት’ ያላቸው ይህ ሙሴ ነው።