Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 5:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሁሉም ተደ​ነቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ኑት፤ እጅ​ግም እየ​ፈሩ፥ “ዛሬ ድንቅ ነገር አየን” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በዚህ ጊዜ ሁሉንም መገረም ያዛቸው፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፣ “ዛሬ እኮ ድንቅ ነገር አየን” እያሉ በፍርሀት ተዋጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሁሉም ተገረሙ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ በፍርሃትም ተሞልተው፦ “ዛሬስ አስደናቂ ነገሮችን አየን፤” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በዚያም የነበሩ ሰዎች ሁሉ እጅግ ተገርመው፥ በመፍራት፥ “ዛሬ ድንቅ ነገር አየን፤” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሁሉንም መገረም ያዛቸው፥ እግዚአብሔርንም አመስግነው፦ ዛሬስ ድንቅ ነገር አየን እያሉ ፍርሃት ሞላባቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 5:26
13 Referencias Cruzadas  

ሕዝቡም አይተው ተደነቁ፤ ለሰውም እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ እግዚአብሔርን አከበሩ።


ሁሉም ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገኑ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነ​ሣ​ልን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና።”


እነ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቀ​ጡ​በት ምክ​ን​ያት ስለ አጡ​ባ​ቸው ገሥ​ጸው ለቀ​ቁ​አ​ቸው፤ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ምር ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበ​ርና።


በጌ​ር​ጌ​ሴ​ኖ​ንም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ሄ​ድ​ላ​ቸው ማለ​ዱት፤ ጽኑ ፍር​ሀት ይዞ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በታ​ንኳ ሆኖ ተመ​ለሰ።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ይህን አይቶ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና፥ “እኔ ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።


ተነሥቶም ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣ፤ ስለዚህም ሰዎች ሁሉ ተገረሙና “እንዲህ ያለ ከቶ አላየንም፤” ብለው እግዚአብሔርን አከበሩ።


እነሆም ነገርኋችሁ።” በፍርሃትና በታላቅ ደስታም ፈጥነው ከመቃብር ሄዱ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሊያወሩ ሮጡ።


ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና “እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን?” አሉ።


ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ል​ሰው አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሣ​ቸ​ውን ዳዊ​ትን ይፈ​ል​ጋሉ፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ቸር​ነ​ቱን ያስ​ቡ​ታል።


ይህ​ችም ከተማ እኔ የም​ሠ​ራ​ላ​ቸ​ውን በጎ​ነት ሁሉ በሚ​ሰሙ፥ እኔም ስላ​መ​ጣ​ሁ​ላ​ቸው በጎ​ነ​ትና ሰላም ሁሉ በሚ​ፈ​ሩና በሚ​ደ​ነ​ግጡ አሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ለደ​ስታ፥ ለክ​ብ​ርና ለገ​ና​ን​ነት ትሆ​ና​ለች።”


ስለ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር።


በዚ​ያም ሀገር ሰው ሁሉ ላይ ፍር​ሀት ሆነ፤ ይህም ነገር ሁሉ በይ​ሁዳ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሁሉ ተወራ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios