Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሴቲ​ቱም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ፣ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሴቲቱ “ጌታ ሆይ! አንተ ነቢይ እንደሆንህ አያለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ “ጌታ ሆይ! አንተ ነቢይ እንደ ሆንክ አሁን ዐወቅሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 4:19
14 Referencias Cruzadas  

ሕዝ​ቡም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት አይ​ተው፥ “ይህ በእ​ው​ነት ወደ ዓለም የሚ​መ​ጣው ነቢይ ነው” አሉ።


የጠ​ራው ፈሪ​ሳ​ዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የም​ት​ዳ​ስ​ሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እን​ዴ​ትስ እንደ ነበ​ረች ባላ​ወ​ቀም ነበ​ርን? ኀጢ​አ​ተኛ ናትና።”


ዳግ​መ​ኛም ዕዉ​ሩን፥ “አንተ ስለ እርሱ ምን ትላ​ለህ? ዐይ​ኖ​ች​ህን ከፍ​ቶ​ል​ሃ​ልና” አሉት፤ እር​ሱም፥ “ነቢይ ነው” አላ​ቸው።


ሁሉም ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገኑ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነ​ሣ​ልን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና።”


ከሕ​ዝ​ቡም ብዙ ሰዎች ይህን ነገር ሰም​ተው “በእ​ው​ነት ይህ ነቢይ ነው” አሉ።


ሕዝቡም “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው፤” አሉ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህ ምን​ድ​ነው?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉት፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊትና በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት በቃ​ሉና በሥ​ራው ብርቱ ነቢ​ይና እው​ነ​ተኛ ሰው ስለ​ነ​በ​ረው ስለ ናዝ​ሬቱ ስለ ኢየ​ሱስ፥


ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ነቢዩ ኤል​ሳዕ ያለ አይ​ደ​ለ​ምን? በእ​ል​ፍ​ኝህ ውስጥ ሆነህ የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንና ቃል​ህን ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እርሱ ይነ​ግ​ረ​ዋል፤” አለ።


እር​ሱም፥ “ያ ሰው ከሰ​ረ​ገ​ላው ወርዶ ሊቀ​በ​ልህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ልቤ ከአ​ንተ ጋር አል​ሄ​ደ​ምን? አሁ​ንም ወር​ቁ​ንና ልብ​ሱን፥ ተቀ​ብ​ለ​ሃል፤ ለወ​ይን ቦታ፥ ለመ​ሰ​ማ​ርያ ቦታና ለዘ​ይት ቦታ፥ ለላ​ሞ​ችና ለበ​ጎች፥ ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ባሮች ይሁ​ንህ።


“የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ የነ​ገ​ረ​ኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፤ እንጃ፥ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ይሆን?”


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስ​ነ​ሣ​ል​ሃል፤ እር​ሱ​ንም ስሙት።


ቀድሞ አም​ስት ባሎች ነበ​ሩሽ፤ ዛሬ አብ​ሮሽ ያለው ግን ባልሽ አይ​ደ​ለም፤ ይህ​ንስ እው​ነት አልሽ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios