እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው ከምድር አራዊት ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበር። እባብም ሴቲቱን “እግዚአብሔር በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ አትብሉ ያላችሁ ለምንድን ነው?” አላት።
ሉቃስ 16:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታውም ዐመፀኛውን መጋቢ እንደ ብልህ ሰው ስለ ሠራ አመሰገነው፤ ከብርሃን ልጆች ይልቅ የዚህ ዓለም ልጆች በዓለማቸው ይራቀቃሉና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታውም አጭበርባሪውን መጋቢ በብልኅነቱ አደነቀው፤ የዚህ ዓለም ልጆች ከመሰሎቻቸው ጋራ በሚኖራቸው ግንኙነት ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታውም ዐመፀኛውን መጋቢ ስለ ብልኃቱ አመሰገነው፤ የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታውም እምነት ያጐደለውን መጋቢ በብልኅነቱ አደነቀው፤ ይህም ከእግዚአብሔር ሰዎች ይልቅ የዓለም ሰዎች በዓለማዊ ኑሮአቸው ብልኆች መሆናቸውን ያሳያል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታውም ዓመፀኛውን መጋቢ በልባምነት ስላደረገ አመሰገነው የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ልባሞች ናቸውና። |
እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው ከምድር አራዊት ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበር። እባብም ሴቲቱን “እግዚአብሔር በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ አትብሉ ያላችሁ ለምንድን ነው?” አላት።
አሁንም የበዓልን ነቢያት ሁሉ፥ አገልጋዮቹንም ሁሉ፥ ካህናቱንም ሁሉ ወደ እኔ ጥሩ፤ ማንም እንዳይቀር፤ ለበዓል ታላቅ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ የቀረውም ሁሉ በሕይወት አይኖርም” አላቸው። ኢዩ ግን የበዓልን አገልጋዮች ያጠፋ ዘንድ በተንኮል ይህን አደረገ።
ኑ፤ እንጠበብባቸው፤ የበዙ እንደሆነ ጦርነት በመጣብን ጊዜ በጠላቶቻችን ላይ ተደርበው በኋላችን ይወጉናልና፥ ከምድራችንም ያስወጡናልና።”
በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።
ሁለተኛውንም፦ ‘አንተሳ ለጌታዬ የምትከፍለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እርሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ስንዴ ነው’ አለው፤ ‘እነሆ፥ ደብዳቤህ፤ ተቀምጠህ ሰማንያ አለብኝ ብለህ ፈጥነህ ጻፍ’ አለው።
የብርሃን ልጆች ትሆኑ ዘንድ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃን እመኑ” ጌታችን ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ሄደ፤ ተሰወራቸውም።
ራሳችሁን አታስቱ፤ ከመካከላችሁ በዚህ ዓለም ጥበበኛ እንደ ሆነ የሚያስብ ሰው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ራሱን ዐላዋቂ ያድርግ።
እነዚህም ፍጻሜያቸው ለጥፋት የሆነ፥ ሆዳቸውን የሚያመልኩ፥ ክብራቸውም ውርደት የሆነባቸው፥ ምድራዊዉንም የሚያስቡ ናቸው።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤