Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ኑ፤ እን​ጠ​በ​ብ​ባ​ቸው፤ የበዙ እን​ደ​ሆነ ጦር​ነት በመ​ጣ​ብን ጊዜ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ላይ ተደ​ር​በው በኋ​ላ​ችን ይወ​ጉ​ና​ልና፥ ከም​ድ​ራ​ች​ንም ያስ​ወ​ጡ​ና​ልና።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ቍጥራቸው እንዳይጨምር፣ ጦርነት ቢነሣ ከጠላቶቻችን ጋራ ዐብረው እንዳይወጉንና ከምድሪቱም ኰብልለው እንዳይሄዱ ዘዴ እንፈልግ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንዳይበዙ፥ ጦርነትም በተነሣብን ጊዜ ጠላቶቻችንን አግዘው እንዳይወጉን ከምድሪቱም እንዳይወጡ ኑ በጥበብ እንምከር።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዚህም የተነሣ ከጠላቶቻችን ጋር ተባብረው ከወጉን በኋላ ከአገሪቱ አምልጠው መሄድ ይችላሉ፤ ስለዚህ ቊጥራቸው እየበዛ እንዳይሄድ ኑ፤ አንድ ዘዴ እንፈልግ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እንዳይበዙ፥ ሰልፍም በተነሳብን ጊዜ ጠላቶቻችንን አግዘው እንዳይወጉን ከምድሪቱም እንዳይወጡ፥ ኑ! እንጠበብባቸው፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 1:10
13 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም ወገ​ኖ​ቻ​ች​ንን ተተ​ን​ኵሎ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን መከራ አጸ​ና​ባ​ቸው፤ ወንድ ልጅ​ንም ሁሉ እን​ዲ​ገ​ድሉ አዘዘ።


“ና ከእኛ ጋር ደምን በማፍሰስ አንድ ሁን፥ ጻድቅ ሰውንም በምድር እንቅበር፥ ብለው ቢማልዱህ፥


በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ውስጥ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አል​ሰ​ሙም።


ኀጢ​አ​ተ​ኞች እነሆ፥ ቀስ​ታ​ቸ​ውን ገት​ረ​ዋ​ልና፥ ፍላ​ጻ​ቸ​ው​ንም በአ​ው​ታር አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋ​ልና፥ ልበ ቅኖ​ቹን በስ​ውር ይነ​ድፉ ዘንድ።


በነ​ጋም ጊዜ አይ​ሁድ ተሰ​ብ​ስ​በው፥ ጳው​ሎ​ስን እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉት ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ ተስ​ማ​ም​ተው ተማ​ማሉ።


ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።


ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን የሲኦል ጕድጓዶችን ይመለከታል።


ጠቢ​ባ​ን​ንም በተ​ን​ኰ​ላ​ቸው ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤ ምክ​ርን የሚ​ጐ​ነ​ጉኑ ሰዎ​ችን አሳብ ያጠ​ፋል።


እነ​ሆም፥ የም​ድ​ሩን ሁሉ ፊት ሸፈነ፤ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያ​ች​ንም ተቀ​ም​ጦ​አል፤ አሁ​ንም ይህ ሕዝብ ከእኔ ይበ​ል​ጣ​ልና ልወ​ጋ​ቸ​ውና ከም​ድ​ሪቱ ላሳ​ድ​ዳ​ቸው እችል እንደ ሆነ፥ ና ርገ​ም​ልኝ፤ አንተ የመ​ረ​ቅ​ኸው ምሩቅ፥ የረ​ገ​ም​ኸ​ውም ርጉም እንደ ሆነ አው​ቃ​ለ​ሁና” ብሎ ይጠ​ሩት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።


የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች ግን በእ​ርሱ ላይ ተቈ​ጥ​ተው፥ “ይህን ሰው ወደ አመ​ጣ​ህ​በት ቦታ መል​ሰው፤ በሰ​ል​ፉም ውስጥ ጠላት እን​ዳ​ይ​ሆ​ነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይ​ው​ረድ፤ ከጌ​ታው ጋር በምን ይታ​ረ​ቃል? የእ​ነ​ዚ​ህን ሰዎች ራስ በመ​ቍ​ረጥ አይ​ደ​ለ​ምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios