ሉቃስ 1:72 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቸርነቱን ከአባቶቻችን ጋር ያደርግ ዘንድ፥ ቅዱስ ኪዳኑንም ያስብ ዘንድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህንም ያደረገው ለአባቶቻችን ምሕረቱን ለማሳየት፣ ቅዱስ ኪዳኑን ለማስታወስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ለአባቶቻችን ምሕረትን አደረገ፤ ቅዱስ ኪዳኑንም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ማድረጉ ለአባቶቻችን ምሕረትን እንደሚያደርግና የተናገረውንም ቅዱስ ቃል ኪዳኑን እንደሚፈጽም በማሰብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደዚህ ለአባቶቻችን ምሕረት አደረገ፤ ለአባታችን ለአብርሃምም የማለውን መሐላውን ቅዱሱን ኪዳን አሰበ፤ |
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤ ይህችንም ምድር ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፤
ዘርህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፤ እስከ ባሕርና እስከ አዜብ እስከ መስዕና እስከ ምሥራቅ ይበዛል፤ ይሞላልም፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ፥ በዘርህም ይባረካሉ።
ነገር ግን በሕፃንነትሽ ወራት ከአንቺ ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳኔን ዐስባለሁ፤ የዘለዓለምንም ቃል ኪዳን አጸናልሻለሁ።
በአንቺ ዘንድ በአለፍሁና በአየሁሽ ጊዜ፥ እነሆ ጊዜሽ እንደ ደረሰ፥ በአንቺም የሚያድሩ ሰዎች ጊዜ እንደ ደረሰ አየሁ። እጆችን በላይሽ ዘረጋሁ፤ ኀፍረተ ሥጋሽንም ከደንሁ፤ ማልሁልሽም፤ ከአንቺም ጋራ ቃል ኪዳን ገባሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ አንቺም ለእኔ ሆንሽ።
ያን ጊዜ እኔ ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ደግሞም ከይስሐቅ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን፥ ከአብርሃምም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ምድሪቱንም አስባለሁ።