ብዙዎች አሕዛብ እርሱን ያደንቃሉ፤ ነገሥታትም አፋቸውን ይዘጋሉ፤ ስለ እርሱ ያልተወራላቸው ያውቁታልና፥ ያልሰሙትም ያስተውሉታልና።
ዘሌዋውያን 7:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ የበደሉን መሥዋዕት በግ በዚያ ያርዱታል፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የበደሉም መሥዋዕት እዚያው ይታረድ፤ ደሙም በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይረጭ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ የበደሉን መሥዋዕት ያርዱታል፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጨዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው እንስሳ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡት እንስሶች በሚታረዱበት ስፍራ ይታረድ፤ ደሙም በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ይረጭ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ የበደሉን መሥዋዕት ያርዱታል፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጨዋል። |
ብዙዎች አሕዛብ እርሱን ያደንቃሉ፤ ነገሥታትም አፋቸውን ይዘጋሉ፤ ስለ እርሱ ያልተወራላቸው ያውቁታልና፥ ያልሰሙትም ያስተውሉታልና።
ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ከርኵሰታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፤ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።
የሚቃጠለውንም መሥዋዕት፥ የኀጢአቱንና የበደሉንም መሥዋዕት ያርዱባቸው ዘንድ፥ በበሩ ደጀ ሰላም በዚህ ወገን ሁለት ገበታዎች፥ በዚያም ወገን ሁለት ገበታዎች ነበሩ።
በመሠዊያውም አጠገብ በመስዕ በኩል በእግዚአብሔር ፊት ያርዱታል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።
በሬውንም በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፤ ደሙንም በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
የኀጢአትን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት በተቀደሰው ስፍራ ጠቦቱን ያርዱታል፤ የበደሉ መሥዋዕት ለካህኑ እንደሚሆን፥ እንዲሁ የኀጢአቱ መሥዋዕት ነውና፤ ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።
እጁንም ለቍርባን በቀረበው ራስ ላይ ይጭናል፤ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በሚቃጠለው መሥዋዕት፥ በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
እጁንም ለቍርባን በቀረበው ራስ ላይ ይጭናል በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ያርደዋል፤ ካህናቱም የአሮን ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
በፍየሉም ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ እርሱ የኀጢአት መሥዋዕት ነውና።
እጁንም በኀጢአት መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፤ ለሚቃጠልም መሥዋዕት እንስሳትን በሚያርዱበት ስፍራ የኀጢአት መሥዋዕት ፍየልዋን ያርዳታል።
እጁንም በኀጢአት መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፤ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ ለኀጢአት መሥዋዕት ያርዳታል።
በተቀደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኀጢአት ዕዳ ይከፍላል፤ አምስተኛውንም እጅ ይጨምርበታል፤ ለካህኑም ይሰጠዋል። ካህኑም በበደል መሥዋዕት አውራ በግ ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
“ስለ ሠራው ኀጢአት የበግ መግዣ ገንዘብ በእጁ ባይኖረው ግን፥ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእግዚአብሔር ያቀርባል። ወደ ካህኑም ያመጣቸዋል፤
ከኀጢአቱም መሥዋዕት ደም በመሠዊያው ግድግዳ ላይ ይረጨዋል፤ የተረፈውንም ደም ከመሠዊያው በታች ያንጠፈጥፋል፤ እርሱ የኀጢአት መሥዋዕት ነውና።
“አሮንንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ የኀጢአት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኀጢአቱ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ይታረዳል፤ እርሱም ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።
በስእለቱ ወራትም ሁሉ ለእግዚአብሔር ይቀደሳል፤ የአንድ ዓመትም ተባት ጠቦት ለበደል መሥዋዕት ያምጣ፤ ስእለቱ ግን ረክሶአልና ያለፈው ወራት ሁሉ አይቈጠርለትም።
የአዲስ ኪዳንም መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ ተረጨው ደሙ ደርሳችኋል።