የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥቡታል። ካህኑም ሁሉን በመሠዊያው ላይ ለቍርባን ያቀርበዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው።
ዘሌዋውያን 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ካህኑም ያመጣዋል፤ ካህኑም ስለ መታሰቢያው ለእርሱ እፍኝ ሙሉ ይዘግናል፤ ለእግዚአብሔርም በእሳት በተቃጠለው ቍርባን ላይ በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል፤ እርሱም የኀጢአት መሥዋዕት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ለካህኑ ያቅርብ፤ ካህኑም ለመታሰቢያ እንዲሆን ዕፍኝ ሙሉ ይዝገንለት፤ በእሳት ከሚቀርበውም ቍርባን በላይ አድርጎ ለእግዚአብሔር በመሠዊያው ላይ በእሳት ያቃጥለው፤ ይህም የኀጢአት መሥዋዕት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ካህኑም ያመጣዋል፥ ካህኑም መታሰቢያው እንዲሆን ከእርሱ እፍኝ ሙሉ ይወስዳል፥ ለጌታም በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ጋር በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፤ እርሱም የኃጢአት መሥዋዕት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱንም አምጥቶ ለካህኑ ይስጠው፤ ካህኑም ከዚያ ዱቄት በእፍኙ ወስዶ ሁሉም ለእግዚአብሔር የቀረበ መሆኑን በማመልከት በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ እርሱም ኃጢአትን የሚያስወግድ መሥዋዕት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ካህኑም ያመጣዋል፥ ካህኑም መታሰቢያው ይሆን ዘንድ ከእርሱ እፍኝ ሙሉ ይውሰድ፥ ለእግዚአብሔርም በእሳት በተቃጠለው ቍርባን ላይ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፤ እርሱም የኃጢአት መሥዋዕት ነው። |
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥቡታል። ካህኑም ሁሉን በመሠዊያው ላይ ለቍርባን ያቀርበዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው።
ከክንፎቹም ይሰብረዋል፤ ነገር ግን አይለየውም። ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ያኖረዋል፤ መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባሉ፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል።
ካህኑም ከተፈተገው እህል፥ ከዘይቱም ወስዶ ከዕጣኑ ጋር መታሰቢያውን ያቀርባል፤ ይህም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።
ወደ ካህኑ ወደ አሮን ልጆች ያመጣዋል፤ ከመልካም ስንዴ ዱቄቱና ከዘይቱም አንድ እፍኝ ሙሉና ነጩንም ዕጣን ሁሉ ወስዶ ካህኑ የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
ካህኑም ከቍርባኑ መታሰቢያውን ይወስዳል፤ በመሠዊያውም ላይ ይጨምረዋል። ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚቃጠል ቍርባን ነው።
ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኵላሊቶቹ ጋር ያመጣሉ።
ስቡ ሁሉ ለደኅንነት መሥዋዕት ከታረደው የበግ ጠቦት ላይ እንደሚወሰድ ስብዋን ሁሉ ይወስዳሉ፤ ካህኑም ለእግዚአብሔር በእሳት በተቃጠለው ቍርባን ላይ በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይሰረይለታል።
“ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ለማምጣት ገንዘብ በእጁ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኀጢአት የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ ክፍል መልካም የስንዴ ዱቄት ለኀጢአት መሥዋዕት ያቀርባል፤ የኀጢአት መሥዋዕት ነውና ዘይት አያፈስስበትም፤ ዕጣንም አይጨምርበትም።
ካህኑም ከእነዚያ በአንዳቸው ስለ ሠራው ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል። የተረፈውም እንደ እህሉ ቍርባን ለካህኑ ይሆናል።”
ካህኑም ከእህሉ ቍርባን መልካሙን የስንዴ ዱቄት ከዘይት ጋር እፍኝ ሙሉ፥ ደግሞም በእህሉ ቍርባን ላይ ያለውን ዕጣን ሁሉ ያነሣል፤ ለእግዚአብሔርም በጎ መዓዛ ያለው የመታሰቢያ ቍርባን እንዲሆን ለመታሰቢያ ነውና በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል።
ካህኑም ከእህሉ ቍርባን አንድ እፍኝ ሙሉ ለመታሰቢያው ወስዶ በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል። ከዚያም በኋላ ለሴቲቱ ያን ውኃ ያጠጣታል።
ወደእርሱም ተመልክቶ ፈራና፥ “አቤቱ፥ ምንድን ነው?” አለ፤ መልአኩም እንዲህ አለው፥ “ጸሎትህም ምጽዋትህም መልካም መታሰቢያ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ዐርጎአል።
ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ።