የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በላያቸውም ያለውን ስብ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ታስቀምጣለህ።
ዘሌዋውያን 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከደኅንነቱም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን አድርገው ያቀርባሉ፤ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኅብረት መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ ቍርባን አድርጎ ያምጣ፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ በሆድ ዕቃው ላይ ያለውን ሥብ ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰላሙም መሥዋዕት ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ የሚያቀርበው፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው መባ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡት ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነው ስብ በሙሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከደኅንነቱም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን አድርጎ ያቀርባል፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ |
የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በላያቸውም ያለውን ስብ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ታስቀምጣለህ።
የበጉንም ስብ፥ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በላያቸውም ላይ ያለውን ስብ፥ የቀኙንም ወርች ትወስዳለህ፤ የሚቀደሱበት ነውና።
እነዚህ ሕዝቦች በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ ልባቸውን አደንድነዋልና፥ ጆሮአቸውንም ደፍነዋልና፥ ዐይኖቻቸውንም ጨፍነዋልና።
አዲስ ልብንም እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።
“ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ከእኔ ዘንድ በሳቱ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዐት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀርባሉ፤ ስቡንና ደሙንም ወደ እኔ ያቀርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በየብልቱም ራሱን፥ ስቡንም ይቈርጡታል፤ ካህናቱም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ይረበርቡታል፤
የአሮንም ልጆች ካህናቱ የተቈረጡትን ብልቶች፥ ራሱንም፥ ስቡንም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ይረበርቡታል።
ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል፤ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። ስቡ ሁሉ ለእግዚአብሔር ነው።
እጁንም ለቍርባን በቀረበው ራስ ላይ ይጭናል፤ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በሚቃጠለው መሥዋዕት፥ በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኵላሊቶቹ ጋር ያመጣሉ።
ለደኅንነት መሥዋዕት ከታረደው ወይፈን እንደ ተወሰደው ይወስዳል፤ ካህኑም ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ያቀርበዋል።
የእርሱ እጆች ለእግዚአብሔር የእሳቱን ቍርባን ያመጣሉ፤ ፍርምባውን በእግዚአብሔር ፊት ቍርባን ያቀርብ ዘንድ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብና የፍርምባውን ስብ ያመጣል።
ካህኑም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል፤ እርሱም የበደል መሥዋዕት ነው።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ከኀጢአቱ መሥዋዕት ስቡንና ኵላሊቶቹን፥ የጉበቱንም መረብ በመሠዊያው ላይ ጨመረ።
ነገር ግን የኀጢአትን ሥጋ ይሽር ዘንድ ከእርሱ ጋር የተሰቀለው አሮጌው ሰውነታችን እንደ ሆነ ይህን እናውቃለን፤ ከእንግዲህ ወዲያ ዳግመና ለኀጢአት እንገዛ ዘንድ አንመለስም።
በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህን እግዚአብሔርንም በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ እንድትወድድ እግዚአብሔር ልብህን፥ የዘርህንም ልብ ያጠራዋል።
ደግሞም ስቡ ሳይጤስ የካህኑ ልጅ መጥቶ የሚሠዋውን ሰው፥ “ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይወስድምና እጠብስለት ዘንድ ለካህኑ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።