Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 29:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የበ​ጉ​ንም ስብ፥ የሆድ ዕቃ​ውን የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ፥ የቀ​ኙ​ንም ወርች ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የሚ​ቀ​ደ​ሱ​በት ነውና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “ከዚህ አውራ በግ ሥቡን፣ ላቱን፣ በሆድ ዕቃው ውስጥ ያለውን ስብ፣ የጕበቱን ሽፋን፣ ሁለቱን ኵላሊቶችና በዙሪያቸው ያለውን ሥብና ቀኙን ወርች ውሰድ፤ ይህ የክህነት አውራ በግ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ለክህነት ሥርዓት የቀረበ አውራ በግ ነውና የበጉን ስብ፥ ላቱን፥ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱን ኩላሊቶቹ፥ በላያቸውም ያለውን ስብና የቀኙን ወርች ትወስዳለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “የሚካኑበት ስለ ሆነ የአውራውን በግ ሞራ ላቱን፥ የውስጥ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሞራ፥ እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን ከሚሸፍነው ሞራ የተሻለውን ክፍል፥ ሁለቱን ኲላሊቶቹን፥ እነርሱን የሚሸፍነውን ሞራና በቀኝ በኩል ያለውን የኋላ እግር ቈርጠህ ለያቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ደግሞም የሚካኑበት አውራ በግ ነውና የበጉን ስብ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች በላያቸውም ያለውን ስብ፥ የቀኙንም ወርች ትወስዳለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 29:22
14 Referencias Cruzadas  

የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ ሁሉ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ያለ​ውን ስብ ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ታስ​ቀ​ም​ጣ​ለህ።


በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ካለው ደም ከቅ​ብ​ዐት ዘይ​ትም ወስ​ደህ በአ​ሮ​ንና በል​ብሱ ላይ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ባሉት በል​ጆ​ቹና በል​ብ​ሶ​ቻ​ቸው ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም ልብ​ሶ​ቹም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆቹ፥ ልብ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ይቀ​ደ​ሳሉ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ሶብ ካለው አንድ የዘ​ይት እን​ጀ​ራና አንድ የቂጣ እን​ጐቻ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤


እነ​ዚ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ለአ​ን​ተና ለል​ጆ​ችህ ሥር​ዐት እን​ዲ​ሆኑ ስለ ተሰጡ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ፍር​ም​ባና ወርች አንተ፥ ከአ​ንተ ጋርም ልጆ​ችህ፥ ቤተ​ሰ​ብ​ህም ተለ​ይቶ በን​ጹሕ ስፍራ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


ካህ​ኑም አን​ዱን ጠቦት ወስዶ ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ያንም አንድ ማሰሮ ዘይት ስለ ልዩ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይለ​የ​ዋል።


ከደ​ኅ​ን​ነ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ ያቀ​ር​ባል፤ ስቡን፥ እስከ ጀር​ባ​ውም ድረስ የተ​ቈ​ረጠ ሙሉ ላቱን፥ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥


ስቡ​ንም ሁሉ፥ ላቱ​ንም፥ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ ሁሉ፥ በአ​ን​ጀ​ቱም ላይ ያለ​ውን ስብ፤


የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህል ቍር​ባን፥ የኀ​ጢ​አ​ትና የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት፥ የቅ​ድ​ስ​ናና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው።


የበ​ሬ​ው​ንና የአ​ው​ራ​ው​ንም በግ ስብ፥ ላቱ​ንም፥ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ ሁለ​ቱን ኵላ​ሊ​ቶ​ቹ​ንም፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ያለ​ውን ስብ፥ የጉ​በ​ቱ​ንም መረብ አመ​ጡ​ለት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አሮን ፍር​ም​ባ​ዎ​ቹ​ንና ቀኝ ወር​ቹን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለየ።


ሥጋ​ውም ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ፍር​ምባ እንደ ቀኙም ወርች ለአ​ንተ ይሆ​ናል።


ወጥ​ቤ​ቱም ወር​ቹን አም​ጥቶ በሳ​ኦል ፊት አኖ​ረው። ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ሳኦ​ልን ለም​ስ​ክር ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ተለ​ይቶ ቀር​ቦ​ል​ሃ​ልና እነሆ፥ በል​ተህ የተ​ረ​ፈ​ህን በፊ​ትህ አኑር” አለው። በዚ​ያም ቀን ሳኦል ከሳ​ሙ​ኤል ጋር በላ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos