በጨለማም ወደ ሶርያውያን ሰፈር ይሄዱ ዘንድ ተነሡ፤ ወደ ሶርያውያንም ሰፈር መጀመሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በዚያ ማንም ሰው አልነበረም።
ዘሌዋውያን 27:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእንስሳህ የሚወለድ በኵር ሁሉ ለእግዚአብሔር ነው፤ ማንም ይለውጠው ዘንድ አይቻለውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእግዚአብሔር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የእንስሳት በኵር ቀድሞውኑ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ፣ ማንም ሰው የእንስሳትን በኵር ለእግዚአብሔር መቀደስ አይችልም፤ በሬም ሆነ በግ የእግዚአብሔር ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ዳሩ ግን ለጌታ የሆነውን የእንስሳ በኵራት ማንም ሰው ሊቀድሰው አይችልም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለጌታ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በኲር ሆኖ የሚወለድ እንስሳ ቀድሞውኑ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንም ሰው የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጎ ሊያቀርበው አይችልም፤ እንቦሳም ሆነ የበግና የፍየል ግልገሎች አስቀድመው ለእግዚአብሔር የተለዩ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር ግን የሚቀርበውን የእንስሳ በኵራት ማንም ይቀድሰው ዘንድ አይቻለውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእግዚአብሔር ነው። |
በጨለማም ወደ ሶርያውያን ሰፈር ይሄዱ ዘንድ ተነሡ፤ ወደ ሶርያውያንም ሰፈር መጀመሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በዚያ ማንም ሰው አልነበረም።
በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
“በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም፥ ከእንስሳም መጀመሪያ የተወለደውን ማሕፀንን የሚከፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይልኝ፤ የእኔ ነው።”
እንዲሁም በበሬዎችህና በበጎችህ፥ በአህያህም ታደርገዋለህ፤ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፤ በስምንተኛውም ቀን ለእኔ ትሰጠዋለህ።
የረከሰም እንስሳ ቢሆን እንደ ግምቱ ይቤዠው፤ በእርሱም የዋጋውን አምስተኛ እጅ ይጨምርበታል፤ ባይቤዥም እንደ ግምቱ ይሸጣል።
ነገር ግን የላሞቹን በኵራት፥ ወይም የበጎቹን በኵራት፥ የፍየሎችንም በኵራት አትቤዥም፤ ቅዱሳን ናቸውና፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፤ ስባቸውንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን መሥዋዕት ታደርገዋለህ።
በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና፤ በግብፅ ምድር በኵርን ሁሉ በመታሁ ቀን ከእስራኤል ዘንድ በኵርን ሁሉ፥ ሰውንና እንስሳን፥ ለእኔ ለይችአለሁ፤ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
“ላምህና በግህ የወለዱትን ተባት የሆነውን በኵራት ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ትቀድሳለህ፤ በበሬህ በኵራት አትሥራበት፤ የበግህንም በኵራት አትሸልት።