እኛ ይህችን ስፍራ እናጠፋታለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና፤ እናጠፋትም ዘንድ እግዚአብሔር ልኮናል።”
ዘሌዋውያን 26:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኮረብታ መስገጃዎቻችሁን አፈርሳለሁ፤ በእጅ የተሠሩ የዕንጨት ምስሎቻችሁንም አጠፋለሁ፤ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኰረብታ መስገጃዎቻችሁን እደመስሳለሁ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁን አፈርሳለሁ፤ በድኖቻችሁን በድን በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየኰረብታው ላይ ያሉአችሁን መስገጃዎች እደመስሳለሁ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁንም አፈራርሳለሁ፤ ሬሳዎቻችሁንም በወደቁት ጣዖቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፤ ፈጽሞ እጸየፋችኋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ የፀሐይ ምስሎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች። |
እኛ ይህችን ስፍራ እናጠፋታለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና፤ እናጠፋትም ዘንድ እግዚአብሔር ልኮናል።”
የእግዚአብሔርም ሰው በመሠዊያው ላይ፥ “መሠዊያ ሆይ፥ መሠዊያ ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ኢዮስያስ የሚባል ልጅ ለዳዊት ቤት ይወለዳል፤ ዕጣንም የሚያጥኑብህን የኮረብታ መስገጃዎቹን ካህናት ይሠዋብሃል፤ የሰዎቹንም አጥንት ያቃጥልብሃል” ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ጠራ።
በቤቴል ባለው መሠዊያ ላይ፥ በሰማርያም ከተሞች ውስጥ ባሉት በኮረብታዎቹ መስገጃዎች ላይ በእግዚአብሔር ቃል የተናገረው ነገር በእውነት ይደርሳልና።”
ኢዮስያስም ዘወር ብሎ በከተማው የነበሩትን መቃብሮች አየ፤ ኢዮርብዓምም በበዓል ጊዜ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል፥ ልኮ ከመቃብሮቹ አጥንቶቹን አስወጣ፥ በመሠዊያው ላይም አቃጠላቸው፥ አረከሰውም። ዘወርም ብሎ ይህን ቃል ወደ ተናገረው ወደ እግዚአብሔር ሰው መቃብር ዐይኖቹን አቀና። እንዲህም አለ፦
በዚያም የነበሩትን የኮረብታውን መስገጃዎች ካህናት ሁሉ በመሠዊያዎቹ ላይ ገደላቸው፥ የሰዎቹንም አጥንት በመሠዊያዎቹ ላይ አቃጠለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ።
ካህናቱንም ሁሉ ከይሁዳ ከተሞች አወጣቸው፤ ከጌባልም ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ካህናት ያጥኑበት የነበረውን የኮረብታ መስገጃ ሁሉ ርኩስ አደረገው። በከተማዪቱም በር በግራ በኩል በነበረው በከተማዪቱ ሹም በኢያሱ በር መግቢያ አጠገብ የነበሩትን የበሮቹን መስገጃዎች አፈረሰ።
የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹንም አደቀቁ፤ የበዓልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት።
ይህም ሁሉ በተፈጸመ ጊዜ በይሁዳ ከተሞች የተገኙ እስራኤል ሁሉ ወጥተው ዐምዶቹን ሰበሩ፤ ዐፀዶችንም ኮረብታዎችንም አፈረሱ፤ መሠዊያውንም አጠፉ። በይሁዳና በብንያምም ሁሉ ደግሞም በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን ፈጽመው እስከ ዘለዓለሙ አጠፉአቸው። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስታቸውና ወደ ከተሞቻቸው ተመለሱ።
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፤ ይህም ኀጢአትን የማስወገድ ፍሬ ሁሉ ነው።
በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለ ምን መታኸን? ፈውስስ ስለ ምን የለንም? ስለ ምን ተስፋ አደረግን? ነገር ግን መልካም ነገር አልተገኘም፤ የፈውስን ጊዜ ተስፋ አደረግን፤ ነገር ግን ድንጋጤ ሆነ።
ምድሬንም በተጠሉ በጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኀጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”
በእጃቸውም አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ የምንዝርናሽንም ስፍራ ያፈርሳሉ፤ ከፍ ያለውንም ቦታሽን ይገለብጣሉ፤ ልብስሽንም ይገፉሻል፤ የክብርሽንም ጌጥ ይወስዳሉ፤ ዕራቁትሽንም ይተዉሻል፤ ቷረጃለሽም።
እንዲህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘለዓለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ መረገጫ ይህ ነው። ዳግመኛም የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በዝሙታቸውና በከፍታዎቻቸው በአለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም።
ሬሳዎቻቸው በጣዖቶቻቸው መካከልና በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ በወደቁ ጊዜ በረዣዥም ኮረብታ ሁሉ፥ በተራሮችም ራሶች ሁሉ፥ በዕንጨቱም ጥላ ሥር ለጣዖቶቻቸው ሁሉ፥ መልካም መዓዛን ባጠኑበት ከቅጠሉ ሁሉ በታች ሬሳዎቻቸው በወደቁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ሥርዐቴንም ብትንቁ፥ ትእዛዛቴንም ሁሉ እንዳታደርጉ፥ ቃል ኪዳኔንም እንድታፈርሱ ሰውነታችሁ ፍርዴን ብትሰለች፥
ጌታ እግዚአብሔር፥ “የያዕቆብን ትዕቢት አረክሳለሁ፤ ሀገሮቹንም ጠላሁ፤ ከተሞቹንም ከሚኖሩባቸው ሰዎች ጋር አጠፋለሁ” ብሎ በራሱ ምሎአልና።
መሳቂያ የሆኑ የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ የእስራኤልም መቅደሶች ባድማ ይሆናሉ፤ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሣለሁ” አለ።