ዳዊትም ቸነፈሩን መረጠ፤ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥዋት እስከ ቀትር ቸነፈርን በእስራኤል ላይ ላከ። ቸነፈሩም በሕዝቡ መካከል ጀመረ፤ ከሕዝቡም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ።
ዘሌዋውያን 26:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቃል ኪዳኔንም በቀል ይበቀልባችሁ ዘንድ ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተማችሁም ትሸሻላችሁ፤ ቸነፈርንም እሰድድባችኋለሁ። በጠላቶቻችሁም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃል ኪዳኔን ስላፈረሳችሁ፣ በላያችሁ ሰይፍ በማምጣት እበቀላችኋለሁ፤ በከተሞቻችሁ ውስጥ በምትሰበሰቡበት ጊዜ ቸነፈር እሰድድባችኋለሁ፤ ለጠላትም እጅ ዐልፋችሁ ትሰጣላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቃል ኪዳኑንም በቀል የሚበቀል ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተሞቻችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ በመካከላችሁም ቸነፈርን እልክባችኋለሁ፤ በጠላትም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእኔ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን በማፍረሳችሁ እናንተን ለመቅጣት ጦርነት አመጣባችኋለሁ፤ በከተሞቻችሁ ብትሰበሰቡም ሊፈወስ የማይችል በሽታ በመካከላችሁ እልካለሁ፤ ለጠላቶቻችሁም እጃችሁን ለመስጠት ትገደዳላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቃል ኪዳኔንም በቀል ይበቀልባችሁ ዘንድ ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተማችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ ቸነፈርንም እሰድድባችኋለሁ፤ በጠላትም እጅ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ። |
ዳዊትም ቸነፈሩን መረጠ፤ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥዋት እስከ ቀትር ቸነፈርን በእስራኤል ላይ ላከ። ቸነፈሩም በሕዝቡ መካከል ጀመረ፤ ከሕዝቡም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ።
“በምድር ላይም ራብ፥ ወይም ቸነፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረማሞ ቢሆን፥ አንበጣ፥ ወይም ኩብኩባ ቢመጣ፥ የሕዝብህም ጠላት ከከተሞቻቸው በአንዲቱ ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥
የሶርያውያንም ሠራዊት ቍጥር ጥቂት ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ብዙውንና ጠንካራውን ሠራዊት አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው፤ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ዘንግተዋልና። በኢዮአስም ላይ ፈረደበት።
እነርሱም፥ “ቸነፈር ወይም ሰይፍ እንዳይጥልብን የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንድንሄድ፥ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ የዕብራውያን አምላክ ጠራን” አሉት።
እኔም ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ ሁላችሁም በሰይፍ ትገደላላችሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገር አደረጋችሁ፤ ያልወደድሁትንም መረጣችሁ እንጂ በጠራኋችሁ ጊዜ አልመለሳችሁልኝምና፥ በተናገርሁም ጊዜ አልሰማችሁኝምና።”
በዚህም ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምክር አፈርሳለሁ፤ በጠላቶቻቸው ፊት በጦርና ነፍሳቸውን በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ፤ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ።
ለእነርሱ፥ ለዘራቸውና ለአባቶቻቸውም ከሰጠኋቸው ምድር እስኪጠፉ ድረስ በመካከላቸው ሰይፍንና ራብን ቸነፈርንም እሰድዳለሁ።”
የአምላካችንን የእግዚአብሔርን በቀል፥ የመቅደሱንም በቀል፥ በጽዮን ይነግሩ ዘንድ ሸሽተው ከባቢሎን ሀገር ያመለጡት ሰዎች ድምፅ ተሰምቶአል።
“ፍላጾችን አዘጋጁ፤ ጕራንጕሬዎችንም ሙሉ፤ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ ቍጣው በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ንጉሥ መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚአብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።
እነርሱና አባቶቻቸውም በአላወቋቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፤ እስከ አጠፋቸውም ድረስ በስተ ኋላቸው ሰይፍን እሰድድባቸዋለሁ።
ሣን። ብላቴናውና ሽማግሌው በመንገዶች ላይ ተጋደሙ፤ ደናግሎችና ጐልማሶች ተማርከዋል፤ በሰይፍም ወድቀዋል፤ በረኃብ ገደልሃቸው፤ በቍጣህም ቀን ሳትራራ አረድሃቸው።
“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ሰይፍን አመጣብሃለሁ፦ ሰውንና እንስሳንም ከአንተ ዘንድ አጠፋለሁ።
“የሰው ልጅ ሆይ! ለሕዝብህ ልጆች ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ጦርን በምድር ላይ በአመጣሁ ጊዜ፥ የምድር ሕዝብ ከመካከላቸው አንድ ሰውን ወስደው ለራሳቸው ጕበኛ ቢያደርጉ፥
ራብንና ክፉዎችን አራዊት እሰድድብሻለሁ፤ እቀሥፍሻለሁ፤ ልጆችሽንም ያጠፋሉ ቸነፈርና ደምም በአንቺ ላይ ይመጡብሻል፤ ሰይፍንም አመጣብሻለሁ፤ ይከቡሻልም። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
ለእስራኤል ተራሮች የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ በላቸው፤ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለምንጮችና ለሸለቆዎች እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ፤ የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ።
በምድራችሁም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፤ ትተኛላችሁ፤ የሚያስፈራችሁም የለም፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድራችሁ አጠፋለሁ።
“በግብፅ እንደ ሆነው ሞትን ሰደድሁባችሁ፤ ጐበዛዝቶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፤ ፈረሶቻችሁንም አስማረክሁ፤ በሰፈራችሁም እሳትን ሰድጄ አጠፋኋችሁ፤ በዚህም ሁሉ እናንተ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።
በሞት እቀጣቸዋለሁ፤ አጠፋቸዋለሁም፤ አንተንና የአባትህን ቤት ግን ለታላቅና ከዚህ ለሚበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ” አለው።
ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ ብሎ ነገራቸው፥ “ከእናንተ መካከል ሰዎችን አስታጥቁ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምድያምን ይበቀሉ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ከምድያም ጋር ይሰለፉ።
በፍርድ ቀን እበቀላቸዋለሁ፤ እግራቸው በሚሰናከልበት ጊዜ፥ የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥ የተዘጋጀላችሁም ፈጥኖ ይደርስባችኋልና።
ሰይፌን እንደ መብረቅ እስላታለሁ፤ እጄም ፍርድን ትይዛለች፤ ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እከፍላለሁ፤ ጠላቶችንም እበቀላለሁ።
ከይሁዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚያህሉ በኢጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሶምሶንን፥ “ገዢዎቻችን ፍልስጥኤማውያን እንደሆኑ አታውቅምን? ያደረግህብን ይህ ምንድን ነው?” አሉት። ሶምሶንም፥ “እንዳደረጉባችሁ እንዲሁ አደረግሁባቸው” አላቸው።