በመምሬ ፊት ያለው ባለ ድርብ ክፍል የሆነው የኤፍሮን እርሻም ለአብርሃም ጸና፤ እርሻው፥ በእርሱም ያለ ዋሻው፥ በእርሻውም ውስጥ በዙሪያውም ያለው ዕንጨት ሁሉ፤
ዘሌዋውያን 2:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህንም ዐሥራት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለበጎ መዓዛ በመሠዊያው ላይ አይቀርቡም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህን የበኵራት ቍርባን አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ማቅረብ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን ሽታው ደስ የሚያሰኝ ቍርባን ሆነው በመሠዊያ ላይ ለመቃጠል አይቀርቡም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህንም የበኵራት ቁርባን አድርጋችሁ ለጌታ ታቀርባላችሁ፤ እንደ መዓዛው ያማረ ሽታ ግን በመሠዊያው ላይ አይቃጠሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየዓመቱ የመከር መጀመሪያ ከእህላችሁ በኲራት አድርጋችሁ የምታቀርቡትንም መባ ለእግዚአብሔር ታመጣላችሁ፤ እርሱ ግን በመሠዊያው ላይ አይቃጠል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህንም የበኵራት ቍርባን አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ እንደ ጣፋጭ ሽታ ግን በመሠዊያው ላይ አይቃጠሉም። |
በመምሬ ፊት ያለው ባለ ድርብ ክፍል የሆነው የኤፍሮን እርሻም ለአብርሃም ጸና፤ እርሻው፥ በእርሱም ያለ ዋሻው፥ በእርሻውም ውስጥ በዙሪያውም ያለው ዕንጨት ሁሉ፤
ይህንም ነገር እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች የእህሉንና የወይኑን፥ የዘይቱንና የማሩንም፥ የእርሻውንም ፍሬ መጀመሪያ ሁሉ ሰጡ፤ የሁሉንም ዐሥራት አብዝተው አቀረቡ።
የሰባቱንም ሱባዔ በዓል ታደርጋለህ፤ እርሱም የስንዴ መከር መጀመሪያ ነው፤ በዓመቱም መካከል የመክተቻ በዓል ታደርጋለህ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ መከሩንም ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤
ከየማደሪያችሁ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ ከሆነ መልካም የስንዴ ዱቄት የተሠራ ሁለት የቍርባን እንጀራ ታመጣላችሁ፤ ከእህላችሁ ቀዳምያት ለእግዚአብሔር በእርሾ ይጋገራል።
መጀመሪያ ከምታደርጉት ሊጥ አንድ እንጎቻ ለይታችሁ ቍርባን ታቀርባላችሁ፤ ከአውድማውም እንደምትለዩት ቍርባን እንዲሁ ትለያላችሁ።
ለእግዚአብሔር ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከስንዴም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤
ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።